ጠ/ሚ ዶክተር አብይ እጩ የካቢኔ አባላትን ለምክር ቤቱ አቅርበው አፀደቁ
አርትስ 06/02/2011
የአዲሱ ካቢኔ አባላት በኢትዮጵያ ብሎም በአፍሪካ ለመጀመሪያ ጊዜ በሚባል ደረጃ 50 በመቶ ሴቶች ናቸው ተብሏል፡፡ ከ20 የካቢኔ አባላት 10ሩ ሴቶች ናቸው፡፡
እነዚህም
1. ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል-የሰላም ሚኒስትር
2. ወይዘሮ ፈትለወርቅ ገብረእግዚአብሄር- ንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር
3 ኢንጂነር አይሻ መሀመድ ሙሳ – የሀገር መከላከያ ሚኒስትር
4 አቶ አህመድ ሽዴ- የገንዘብና ኢኮኖሚ ሚኒስትር
5 አቶ ኡመር ሁሴን- የግብርና ሚኒስትር
6 ወይዘሮ አዳነች አቤቤ- የገቢዎች ሚኒስትር
7 ዶክተር ኤርጉጌ ተስፋዬ- የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር
8 ዶክተር ፍፁም አሰፋ- የፕላንና ልማት ኮሚሽን ሚኒስትር
9. ዶ/ር ሂሩት ወ/ማርያም ሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር
10. ዶ/ር ጥላዬ ጌቴ የት/ት ሚኒስትር
11. ወ/ት የአለም ፀጋዬ የሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ሚኒስትር
12. ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ የትራንስፖርት ሚኒስትር
13. ዶ/ር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር
14. አቶ ዣንጥራር አባይ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስትር
15. ዶ/ር ሳሙኤል ሁርጶ ማዕድንና ነዳጅ ሚኒስትር
16. ዶ/ር ሂሩት ካሳ ባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ሆነዋል፡፡
ባሉበት የሚቀጥሉ ሚኒስትሮች የጤና ጥበቃ፣ ውጭ ጉዳይ፣ ውሃ መስኖና ኢነርጂ ናቸው፡፡