loading
ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን 37ኛውን ዓለማቀፍ መንፈሳዊ ጉባኤ ማካሄድ ጀመረች

አርትስ 05/02/2011

ቤተ ክርስቲያኒቱ በየዓመቱ ጥቅምት ወር ላይ የምታካሂደው ይህ ጉባኤ፥ በሀገር ውስጥ 50 ሀገረ ስብከቶችን እና በውጭ ያሉትን 11 ሀገረ ስብከቶችን በማካተት ነው እየተካሄደ የሚገኘው፡፡
በጉባዔው የሁሉም ሀገረ ስብከት ተወካይ ጳጳሳት ሪፖርት የሚያቀርቡበትና ለቀጣይ ዘመንም የስራ እቅድና የአቋም መግለጫ የሚወጣበት ነው፡፡
በጉባኤው ላይ የቤተክርስቲያኒቷ ፓትሪያርክ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲዎስና ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሪዮስ ተገኝተዋል በጋራ የተገኙበት መሆኑ የዘንድሮውን ልዩ ያደርገዋል።
በጉባኤው ላይ ብጹዓን ሊቃነ ዻዻሳት የሀገር ሽማግሌዎችና ካህናት እንዲሁም ምዕመናን የተገኙ ሲሆን በዚህ ሳምንት መጨረሻ ዓርብ ይጠናቀቃል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *