ኢትዮጵያ በተያዘው ዓመት የ8.5 በመቶ እድገት እንደምታስመዘግብ የዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም ተነበየ
አርትስ 18/01/2011
የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ባለፈዉ ዓመት 7.5 በመቶ ዕድገት ማሳየቱን የጠቆመዉ ተቋሙ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አቢይ አህመድ ወደ ስልጣን መምጣታቸዉን ተከቶሎ በኢኮኖሚ ረገድ ያደረጉዋቸዉ ማሻሻያዎች ኢኮኖሚዉ ዳግም እንዲነቃቃ ምክንያት መሆኑን ጠቁሟል፡፡
በሰላም እጦት ምክንያት ለዘመናት ሻክሮ የነበረዉን የኢትዮ-ኤርትራ ግንኙነት ጉዳይ እልባት እንዲያገኝ በማድረግና የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ዳግም በማደስ፤ በመንግስት ቁጥጥር ስር የነበሩ ትላልቅ የመንግስት ኩባንያዎችን ለባለሃብቶች ክፍት ማድረጋቸዉንና በቀጠናዉ የተፈጠረዉ አለመረጋጋት በዲፕሎማሲያዊ መንገድ ለመፍታት ጥረት ማድረጋቸዉን ለዕድገቱ መሻሻል አስተዋፅኦ እንደሚኖረው በሪፖርቱ ተመልክቷል፡፡
የዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም ቡድን መሪ ጁሊዮ እስካላኖ የዳሳሰ ጥናቱ ተመርኩዘው ይፋ እንዳደረጉት ሀገሪቱ ከባለፈዉ ዓመት በተሻለ የዕድገት ለዉጥ ያሳየችዉ የሀገር ዉስጥና የዉጭ ባለሃብቶችን በማሳተፏም ነው፡፡
ኢትዮጵያ የሎጂስትክስ ኢንዳስትሪዉን ለዉጭ ኩባንያዎች በሽርክና ለመሸጥ መስራት እንደምትፈልግ መግለፅዋም የሚታወስ ነዉ፡፡
መንግስት ከሀገር ዉስጥ ኢኮኖሚ የመበደር አቅምን መቀነስ፤የዋጋ ንረትን መቀነስ፤የወጪ ንግድ በመጨመር ኢኮኖሚዉን ማነቃቃት አስፈላጊ መሆኑንንም በሪፖርቱ አመልክቷል፡:
ኢ.ቢ.ሲ