የአዲስ አበባ ም/ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ እኛ ኢትዮጵያውያን እንደደመራ የምናበራ ብዙ ሀብት ያለን ህዝቦች ነን አሉ
አርትስ 16/01/2011
ዛሬ የደመራ በዓል ተከብሯል። የዘንድሮው በዓል በአዲስ አበባ ሲከበር ለኢተዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ን ከሁለቱ ሲኖዶሶች መዋሀድ ጋር ተይይዞ ሁለቱም ብፁአን አባቶች የተገኙበት መሆኑ የተለየ አድርጎታል።
በበአሉ ላይ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ ፣የአዲስ አበባ ም/ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ እና ካቢኔያቸው እንዲሁም ከአገር ውስጥና ከውጭ እንግዶች ተገኝተዋል።
የአዲስ አበባ ም/ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ እኛ ኢትዮጵያውያን እንደ ደመራ የምናበራ ብዙ ሀብት ያለን በቀላሉ የማይበተኑ ሀብቶች ያሉን ህዝቦች ነን ብለዋል። ከንቲባው በንግግራቸው መስቀል የፍቅር፣ የሰላምና የአንድነት ምልክት መሆኑን አፅንኦት ሰጥተውታል።
የመስቀል በዓል የፍቅርና የሰላም እንዲሆን የሃይማኖት አባቶች እንዲፀልዮ አሳስበዋል።
የደመራ በዓል በአዲስ አበባ በተለያዩ ሃይማኖታዊ ስነስርዓቶች ተከብሯል።