ሞሮኮና አልጀሪያ ህገ ወጥ ስደትን ለማስቆም የፋይናንስ እጥረት ፈተና ሆኖባቸዋል
አርትስ 10/01/2011
ሁለቱ የሰሜን አፍሪካ ሀገሮች እየተባባሰ የመጣውን ህገ ወጥ ስደት ለመከላከል በጋራ እንሰራለን ቢሉም የኢኮኖሚ አቅማቸው እንቅፋት ሆኖባቸዋል፡፡
የፈረንሳዩ ሳምንታዊ መጽሄት ኤል ኤክስፕረስ እንደዘገበው የፓሪስ መንግስት ሞሮኮና አልጀሪያን ጥረታቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ዓለም አቀፍ ድጋፍ እንዲደረግላቸው ጥሪ አቅርቧል፡፡
የፈረንሳይ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ዠራርድ ኮሎምቦ ከመጽሄቱ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልለስ ሁለቱን ሀገሮች እንደ መሸጋገሪያ ተጠቅመው ወደ አውሮፓ የሚገቡትን ስደተኞች ለማስቆም በፋይናንስ ልንደግፋቸው ይገባል ብለዋል፡፡
ባለፉት 8 ወራት ብቻ ከሞሮኮ ተነስተው በስፔን በኩል አቋርጠው ወደ አውሮፓ የገቡት ህገ ወጥ ስደተኞች ቁጥር 33 ሺህ 795 መሆኑ የችግሩን ስፋት ያሳያል ብለዋል ኮሎምቦ፡፡