ለዓለም ድህነት መባባስ የአፍሪካ የህዝብ ቁጥር መጨመር አንዱ ምክንያት ነው ተባለ
አርትስ 8/1/2011
ሮይተርስ እንደዘገበው በአፍሪካ በፍጥነት እየጨመረ ያለው የህዝብ ቁጥር ለአህጉሪቱም ሆነ ለዓለም ድህነትን ለማጥፋት ትልቅ ፈተና ሆኗል፡፡
ባለፉት 20 ዓመታት በቢሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ራሳቸውን ከድህነት ቢያላቅቁም አሁንም በአፍሪካ ያለው ፈጣን የህዝብ እድገት የድሆችን ቁጥር ለመቀነስ እንቅፋት ነው ተብሏል፡፡
የቢል ጌትስ ፋውዴሽን በጥናት ደረስኩበት እንዳለው በዓለማችን ፈጣን የህዝብ እድገት በሚታይባቸው የአፍሪካ ሀገሮች የድህነት መጠኑም በዚያው ልክ ይጨምራል፡፡
በጥናቱ መሰረት በፈረንጆቹ 2050 በዓለማችን የድሃ ድሃ ከሚባሉት ሰዎች መካከል 40 በመቶ የሚሆኑት በዲሞክራቲክ ኮንጎና በናይጀሪያ እንደሚኖሩ ይጠበቃል፡፡