የጊኒው ፕሬዝዳንት ልጅ ንብረት በብራዚል ተይዟል
አርትስ 07/01/2011
የኢኳቶሪያል ጊኒው ምክትል ፕሬዝዳንት ቴውዶሪን ኦቢያንግ ንጉየማ የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ልጅ ናቸው፡፡
ሰሞኑን በህክምና ሰበብ 11 ልኡካንን አስከትለው ወደ ብራዚል ያቀኑት ምክትል ፕሬዝዳንቱ የብራዚልን የገንዘብ ዝውውር ህግ ጥሰው ነው ንብረታቸው በፖሊስ የተያዘው፡፡
ቢቢሲ እንደዘገበው ወደ ብራዚል ከ2 ሺህ 500 ዶላር በላይ ይዞ መግባት አይቻልም፡፡ ኦቦያንግ ግን 1.5 ሚሊዮን ዶላር ጥሬ ገንዘብ እና በ17 ሻንጣዎች የተሞሉ ውድ የቅንጦት ሰዓቶች እንዲሁም አልባሳት ይዘው በመግባታቸው ሁሉም ንብረቶች በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡
የ48 ዓመቱ ኦቢያንግ ዝነጣ የሚያበዙና ፍልጎታቸው በቀላሉ የማይረካ ስመሆናቸው በሰፊው ይነገርላቸዋል፡፡
በአሁኑ ጊ ጊዜ ከአባታቸው ጋር ሆነው የሚመሯት ኢኳቶሪያል ጊኒ በነዳጅ ዘይት የበለጸገች ሀገር ብትሆንም 70 በመቶ የሚሆኑት ዜጎቿ በድህነት ውስጥ ነው የሚኖሩት፡፡
ምክትል ፕሬዝዳንቱ በየሄዱበት ንብረታቸው መያዙ ልማዳቸው ነው፡፡ ባለፈው ዓመት ስዊዘርላንድ 11 ቅንጡ አውቶሞቢሎችን ወርሳቸዋለች፡፡
ፈረንሳይ ደግሞ በ2017 ፍራንስ ውስጥ የሚገኘውን ውድ ቤታቸውን ጨምሮ ንብረቶቻቸው እንዳይንቀሳቀሱ እንዲሁም 35 ሚሊዮን ዶላር ቅጣት ወስናባቸዋለች፡፡