loading
በቤኔሻንጉል ጉሙዝ ክልል በተከሰተው ግጭት የተጠረጠሩ 40 ሰዎች ቁጥጥር ስር ዋሉ 

አርትስ 07/01/2011
በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል በአልመሃል ቀበሌ እና በጉባ ወረዳ ግጭት ተከስቶ በዚህም ምክንያት ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ የሰዎች ህይወት ማለፉን እና ንብረት መውደሙን የዓይን እማኞች እና የክልሉ መንግስት አረጋግጠዋል፡፡
ግጭቱ የተነሳበት አካባቢ ሰፊ የእርሻ ኢንቨስትመንት ቦታ መሆኑን እና ለሰራተኞች ደመወዛቸውን በወቅቱ ያለመክፈል እና የመብት አያያዝ ችግሮች መኖራቸው በመረጋገጡ ለማስተካከል ጥረት እየተደረገ ባለበት ወቅት ከስፍራው ግጭት መነሳቱን እና በዚህም ጉዳት መድረሱን የቤኔሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት ኮሚዪኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ ዘላለም ጃለታ ተናግረዋል፡፡
የአካባቢው ነዋሪዎችም ዳግም ግጭት ይነሳል በሚል ስጋት ላይ ቢሆኑም የክልሉ ልዩ ኃይል እና የአካባቢው ፖሊስ አባላት ዳግም የከፋ ጉዳት እንዳይደርስ እየሰሩ ነው ሲል የአማራ ብዙሃን መገናኛ ዘግቧል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *