የአሜሪካ ልዩ ሀይል ከግብጽ ጦር ጋር የጋራ ጸረ ሽብር ልምምድ ጀምሯል
አርትስ 02/13/2010
የግብጽ ወታደራዊ ቃል አቀባይ ኮሎኔል ታሜር አል ሪያፊ የልምምዱ ዓላማ ከአሜሪካ ልዩ ሀይል ጋር ሞያዊ ልምድ ለመለዋወጥ ነው ብለዋል፡፡
ሚድል ኢስት ሞኒተር እንደዘገበው የጸረ ሽብር ልምምዱ የተጀመረው የግብጽና የአሜሪካ ጦር “ኦፕሬሽን ብራይት ስታር” የተሰኘወን ወታደራዊ ልምምድ ከመጀመራቸው 2 ቀናት ቀደም ብሎ ነው፡፡
ልምምዱ በዋናነት ሽብርተኞችን በአየርም ሆነ በምድር እንዴት መዋጋት እንደሚቻል፣ እንዲሁም የባህር ላይ ጥቃትን ያካተተ ነው ብለዋል ቃል አቀባዩ፡፡
“ኦፕሬሽን ብራይት ስታር” የተሰኘው ዋናው ወታደራዊ ልምምድ ከነገ ጀምሮ ለ12 ቀናት የሚቆይ ሲሆን ከአውሮፓ፣ከመካከለኛው ምስራቅና ከአፍሪካ የተውጣጡ ሀገራት ይሳተፉበታል ተብሏል፡፡