የአፍሪካ ቻይና ግንኙነት መሰረቱ እንደጸና ቀጥሏል ተባለ፡፡
የዲሞክራቲክ ኮንጎ ፕሬዝዳንት ዴኒስ ሳሶ ንጎየሶ እንዳሉት ቻይና በምትገነባው ቤልት ኤንድ ሮድ ፕሮጀክት አፍሪካ መሳተፏ በሁለቱ ወገኖች መካከል ያለውን የጋራ እድገት ያፋጥነዋል፡፡
ሮይተርስ እንደዘገበው ከተባበሩት መንግስታት የ2030 የልማት አጀንዳ ጋር ተጣጥሞ እየተካሄደ ያለው ይህ ኢኒሸቲቭ ከአፍሪካ ህብረት የ2063 እቅድ ጋርም የተሰናሰለ ነው ብለዋል ፕሬዝዳንቱ፡፡
ቤልት አንድ ሮድ ፕሮጀክት አፍሪካን ከቀሪው ዓለም ጋር በኢኮኖሚ ያስተሳስራታል ያሉት ንጎየሶ የቻይና አፍሪካ የትብብር ፎረም አፍሪካና ቻይና ይበልጥ ተቀራርበው እንዲሰሩ ትልቅ ሚና አለው ብለዋል፡፡
የትብብር ፎረሙ ጉባኤ “ለጋራ ልማትና ብልጽግና በጋራ መስራት በሚል መሪ ሃሳብ”
በፈረንጆቹ መስከረም መጀመሪያ ላይ በቻይናዋ መዲና ቤጂንግ ይካሄዳል፡፡
አርትስ 23/12/2010