የቀድሞ የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አብዲ መሐመድ ኡመር በአዲስ አበባ ውስጥ በቁጥጥር ስር ዋሉ
ፋና እንደዘገበዉ አቶ አብዲ መሐመድ ኡመር በቁጥጥር ስር የዋሉት በዛሬው እለት አዲስ አበባ አትላስ አካባቢ በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ውስጥ ነው።
የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ምክር ቤት በትናንትናው እለት ባካሄደው አስቸኳይ የአቶ አብዲ መሐመድ ኡመር ያለመከሰስ መብት ማንሳቱ ይታወሳል።
የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ምክር ቤት ከአቶ አብዲ በተጨማሪ የ6 የምክር ቤት አባላትን ያለመከሰስ መብትን አንስቷል።