በአለም አቀፍ ደረጃ የሚሰሩ ሆቴሎች ባህልን የሚያንፀባርቅ ገፅታ ሊኖራቸዉ ይገባል ተባለ
ይህ የተባለዉ የካፒታል ኢንተርናሽናል ሆቴል የባህል አዳራሹን ሲያስመርቅ ነው፡፡
በካፒታል ሆቴል የባህል አደራሽ ምረቃ ስነ-ስርዓት ላይ የከተማዋ ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ እና ምክትል ከንቲባ ዳግማዊት ሞገስ የተገኙ ሲሆን ምክትል ከንቲባዋ ዳግማዊትም ከተማችን አዲስ አበባ ብዙ ባህል አዳራሾች ያስፈልጓታል ፤በባህል ላይ የሚሰሩ ባለሀብቶችንም እናበረታታለን ብለዋል፡፡
የካፒታል ሆቴል ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አዲስአለም ገብሬ በሆቴላቸዉ ዉስጥ ልዩ የባህል አዳራሽ መሰራቱ ለተለያዩ ጉዳዮች ወደ ሀገር ዉስጥ የሚገቡ ዲፕሎማቶችና ቱሪስቶች የሀገራችንን ባህል በአንድ ቦታ በቀላሉ እንዲያዉቁት ለማድረግ ያስቸላል ብለዋል፡፡
የባህል አዳራሹ ከ 20 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነባ ሲሆን የመላው ብሄርብሄረሰብ ባህላዊ ምግቦችን ያቀርባል፡፡ የባህል አዳራሹ ኢትዮጲያ ያሏትን ባህላዊ እና ታሪካዊ ቅርሶች እንዲያሳይ ተደርጎ የተቀረጸ ነው፡፡
አዳራሹ ብቻ ለ40 ሰዉ የስራ እድል ይፈጥራል ተብሏል፡፡