loading
ሰሜን ኮሪያ የሮኬት ማስወንጨፊያ ጣቢያዎቿዋን ማፍረስ መጀመሯ ተሰማ

የሳተላይት ምስል እንደሚያሳየው ፒዮንግያንግ ቁልፍ የሮኬት ማስወንጨፊያ ጣቢያዎቿን እያፈረሰች መሆኗ ተረጋጋጧል፡፡
ቢቢሲ እንደዘገበው በተችዎቻቸው ዘንድ መቆሚያ መቀመጫ ላጡት ለፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ይህ ትልቅ እፎይታ ነው፡፡
በሁኔታው የተደሰቱት ትራምፕም እኔ ያላልኩትን የሚያራግቡና የሀሰተኛ ወሬ የሚያናፍሱ በሰሜን ኮሪያ ድርጊት ተበሳጭቷል ለሚሉ ሁሉ ይሄው እኔ ደስተኛ ነኝ የሚል ጽሁፍ በትዊተር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡
ይሁንና የአሜሪካ ባለስልጣናት ሰሜን ኮሪያ የምታፈርሰው የትኛውን የኒውክሌር ጣቢያ እንደሆነ ስላልተገለጸ አሁንም በኪም ላይ ጥርጣሬ አላቸው ይላል ዘገባው፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *