በግሪክ በተቀሰቀሰ ሰደድ እሳት በርካቶች ህይወታቸውን አጥተዋል
በቦታው የተሰማሩ የነፍስ አድን ሰራተኞች እንዳሉት በዋና ከተማዋ አቴንስ አቅራቢያ በተከሰተው አደጋ እስካሁን 49 ሰዎች ሞተዋል፡፡
ቢቢሲ እንደዘገበው ከሟቾቹ መካከል ህጻናት የሚበዙ እንደሆነ ታምኗል፡፡
ሲ ኤን ኤን በዘገባው እንዳሰፈረው በግሪክ እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ከ2007 ወዲህ እንደዚህ ዓይነት የከፋ የእሳት አደጋ አጋጥሞ አያውቅም፡፡
ከሟቾቹ በተጨማሪ 156 ሰዎች የመቁሰል አደጋ ደርሶባቸዋል ተብሏል፡፡
ከነዚህ መካከል ደግሞ አስራ አንዱ ጉዳታቸው በጣም ከባድ በመሆኑ የተለየ ክትትል እየተደረገላቸው መሆኑን ዘገባው አመላክቷል፡፡