የተሰናባቹ የአሜሪካ ፕሬዜዳንት ዶናልድ ትራምፕ የኮሮናቫይረስ ልዩ አማካሪ የሆኑት ዶክተር
አዲስ አበባ፣ ህዳር 22፣ 2013 የተሰናባቹ የአሜሪካ ፕሬዜዳንት ዶናልድ ትራምፕ የኮሮናቫይረስ ልዩ አማካሪ የሆኑት ዶክተር ስኮት አትላስ የስራ መልቀቂያ አስገቡ፡፡ የፕሬዜዳንቱ የኮሮናቫይረስ ልዩ አማካሪ የሆኑት ዶክተር ስኮት አትላስ በገዛ ፈቃዳቸውን ስራ መልቀቃቸውን የዋይት ሃውስ ባለስልጣናት ተናግረዋል፡፡
የኮቪድ 19 በመከላከል ዙሪያ ከተቀሩት የግብረ ሃይል አባላት ጋር አራት ወራትን ከፈጀ ንትርክ በኋላ የስራ መልቀቂያ ማስገባታቸው ነው የተነገረው፡፡የአትላስ ስራ መልቀቂያ ደብዳቤ ማስገባታቸውን በመጀመሪያ የዘገበው ፎክስ ኒውስ ነው፡፡ ልዩ አማካሪው በደብዳቤያቸው ስራዬን በልዩ ትኩረትና በጥንካሬ ስሰራ ቆይቻለሁ ብለዋል፡፡
ዘወትር ምክሬ የነበረው የቫይረሱን ስርጭት መግታት እና ጉዳቱን መቀነስ ላይ ሲሆን ሰራተኛና ደሃው ላይ ያተኮረ የጤና ፖሊሲ እንዲወጡ ማስቻል ነበረ ብለዋል ልዩ አማካሪው፡፡ የተላላፊ በሽታዎች ከፍተኛ ኤክስፐርት አንቶኒ ፋውቺ በግሌ ከዶክተር አትላስ ጋር ግጭት አልነበረንም ነገር ግን በአቋም እንለያይ ነበር ማለታቸውን ሲጂቲኤን ዘግቧል፡፡