ግብፃዊው ታዳጊ በሰራው ጀግንነት የጣሊያን ዜግነት ሊሰጠው ነው፡፡
ግብፃዊው ታዳጊ በሰራው ጀግንነት የጣሊያን ዜግነት ሊሰጠው ነው፡፡
የ13 ዓመቱ የግብፅ ተወላጅ ባለፈው ጣሊያን ውስጥ ትምህርት ቤት በሚያመላልሳቸው ሾፌር አደጋ ሊድርስባቸው የነበሩ 51 ህፃናትን በጥበቡ ታድገዋቿል፡፡
ሚድል ኢስት ሞኒተር እንደዘገበው አሽከርካሪው በአውቶቡሱ ውስጥ የነበሩትን ተማሪዎች ስልካችሁን አስረክቡ ሲላቸው እሱ ግን ስልኩን ደብቆ ነው ወደ አባቱ ይደውል ነበር፡፡
አባቱም ወዲያውኑ ለፖሊስ በመደወላቸው በፍጥነት ወደ ስፍራው ሄደው ህፃናቱን ከሞት የማትረፍ ስራን ሰርተዋል፡፡
ራሚ ሺሀታ የተባለው ይህ ታዳጊ በዓረብኛ ቋንቋ የሚፀልይ በማስመሰል ለአባቱ ስልክ በመደወል ነበር እራሱን እና ጓደኞቹን በእሳት ከመቃጠል ማዳን የቻለው፡፡
የጣሊያን ፖሊስ የታዳጊው ዘዴ ተዓምር የሚባል ነው፤ ይህ ባይሆን ኖሮ አሰቃቂ እልቂት ይፈጠር ነበር ብል በመግለጫው፡፡
ታዳጊው ሺሀታ ጠሊያን ውስጥ ቢወለድም 18 ዓመት ያልሞላው ውጭ ሀገር ዜጋ ተወላጅ ዜግነት አያገኝም በሚለው የሀገሪቱ ህግ መሰረት እስከ ዛሬ የጣሊያን ዜግነት የለውም፡፡
አሁን ግን ለሰራው ጀግንነት ምስጋና ይግባውና የጣሊያን መንግስት ከልዩ ምስጋና ጋር ዜግነት ሊሰጠው መሆኑ ተሰምቷል፡፡
የታዳጊው አባትም “ልጀ ግዴታውን በሚገባ ተወጥቷል በማለት” እንደኮሩበት ተናግረው ዜግነት ሊሰጠው መሆኑ ጥሩ ስሜት እንደፈጠረባቸው ገልፀዋል፡፡
መንገሻ ዓለሙ