loading

በሙምባይ ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ውጤታማ ሁነዋል

የታታ ሙምባይ ማራቶን 2019 በዛሬው ዕለት በህንዷ ሙምባይ ከተማ ተካሂዷል፡፡
በውድድሩ በሴቶች የተካሄደውን ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ተከታትለው በመግባት ሲያሸንፉ፤ ወርቅነሽ አለሙ 2፡25፡45 በመግባት ቀዳሚ ስትሆን፣ አማኔ ጎበና በ2፡26፡09 ሁለተኛ እንዲሁም ብርቄ ደበሌ በ2፡26፡39 ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቅቃለች፡፡
በወንዶች ደግሞ ኬንያዊው ኮስማስ ላጋት ኢትዮጵያውያን አትሌቶችን አስከትሎ በመግባት አሸንፏል፡፡ የገባበት ሰዓት 2፡09፡15 ሲሆን ኢትዮጵያዊው አትሌት አይቼው በንቲ 2፡10፡05 ጊዜ ሁለተኛ፣ ሹመት አካልነህ በ2፡10፡14 ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቅቀዋል፡፡
ከውድድሩ አስቀድሞ ባለው ጥሩ ሰዓት፤ የአሸናፊነት ግምት ተሰጥቶት የነበረው ኢትዮጵያዊው አበራ ኩማ በ2፡13፡10 ሰባተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቅቋል፡፡
የታታ ሙምባይ ማራቶን በየዓመቱ የፈረንጆቹ ጥር ወር በገባ በሶስተኛው ዕሁድ የሚከናወን ሲሆን አሸናፊ የሚሆነው አትሌት 405.000 ዶላር የሚሸለምበት ነው፡፡
የውድድሩ ክብረወሰን በወንዶች በኬንያዊው አትሌት ጌዲዮን ኪፕኬተር በ2፡08፡35 በ2016 በማሸነፍ ቀዳሚ ሲሆን፤ በሴቶች ቫለንቲን ኪፕኬተር በ2013 በ2፡24፡33 ጊዜ በሆነ ክብረወሱኑን በስሟ አስመዝግባለች፡፡
ውድድሩ በእስያ በተሳታፊ ቁጥር ብዛት ቀዳሚ እንደሆነ ይነገርለታል፡፡

በሌሎች ሀገራት ውድድሮች በአሜሪካ የሂውስተን ግማሽ ማራቶን ሲከናወን በወንዶች ኢትዮጵያውያኑ ሹራ ኪጣታ በ1:00:11 እና ጀማል ይመር በ1:00.14 ጊዜ አንደኛና ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ ሲያጠናቅቁ ፤ በሴቶች ሩቲ አጋ ሶስተኛ ሆናለች። በስፔን የማድላ ሃይፋ ግማሽ ማራቶንደግሞ በወንዶች 1ኛ ገብሬ እርቅ ይሁን በ1:03.20 ሲወጣ ፣ጥሩነህ ቢረሳው በ1:03.54 ሰዓት ሁለተኛ ሁኗል ። በሴቶች አበበች ሙሉጌታ በ1:11.05 ሰዓት አሸነፊ በመሆን አጠናቅቃለች ።

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *