loading
321 የቡራዩ ተጠርጣሪዎች ከእስር ሲቀለቀቁ 109 ደግሞ ክስ ተመሰረተባቸው።530 ታራሚዎች ይቅርታ ተደርጎላቸዋል

የፌዴራል ዐቃቢ ህግ በሰጠው መግለጫ በያዝነው ዓመት መጀመሪያ ላይ በቡራዩ ከተማ በተቀሰቀሰው ጥቃት ተሳትፈዋል ባላቸው 109 ተጠርጣሪዎች ላይ ክስ መመስረቱን ተናግሯል።

ከነዚህም መካከል 81 ተጠርጣሪዎች በተገኙበት 28ቱ ደግሞ በሌሉበት ክስ የተመሰረተባቸው መሆኑን ነው የአቃቤ ህግ መግለጫ የሚያስረዳው፡፡

በቁጥጥር ስር ያልዋሉትን 28 ተጠርጣሪዎች ፖሊስ ለማደን የፍርድ ቤት ማዘዣ እንደወጣባቸው በመግለጫው ተካቷል፡፡

የፌዴራል አቃቤ ህግ የህዝብ ግንኙነት ዳሬክተር አቶ ዝናቡ ቱኑ በመግለጫቸው እንዳሉት ቀደም ሲል በጉዳዩ ተጠርጥረው በቁጥጥር ከዋሉት 649 ተጠርጣሪዎች መካከል 321 የሚሆኑት በወንጀሉ ለመሳተፋቸው ማስረጃ ባለመገኘቱ በነጻ ተለቀዋል ፡፡

የምህረት አዋጁ ተግባራዊ መደረግ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ከ13 ሺህ በላይ ፍርደኞችም ጉዳያቸው ተመርምሮ የአዋጁ ተጠቃሚ በመሆን ሰርተፊኬት ማግኘት ችለዋል፡፡

መጪውን የገና በዓል ምክንያት በማድረግ ለ530 የህግ ታራሚዎች ይቅርታ መደረጉን  የፌዴራል አቃቤ ህግ ያስታወቀ ሲሆን፤ህጻናትን ይዘው የታሰሩ እናቶች እና እድሜያቸው ከ60 በላይ የሆኑ ታማሚ አረጋዊያን የእድሉ ተጠቃሚ ሆነዋል ተብሏል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *