loading
በትግራይ መሠረታዊ አገልግሎቶች እንዲጀመሩ የደኅንነት ማረጋገጫ መሰጠቱ ተገለጸ::

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 27፣ 2014 የትግራይ ክልል ፕሬዝዳንት ደብረጽዮን ገብረ ሚካኤል የተቋረጡ መሠረታዊ አገልግሎቶችን በሚመለከት ለፌደራል መንግሥት የደኅንነት ዋስትና ደብዳቤ መላካቸው ተነግሯል፡፡ ይህ የተገለጸው የህወሓት ከፍተኛ አመራሮች ከአሜሪካ እና ከአውሮፓ ኅብረት ልዩ መልዕክተኞች እና ከምዕራባውያን አምባሳደሮች ጋር በመቐለ ከተገናኙ በኋላ መሆኑን ኦል አፍሪካን ዶት ኮም ዘግቧል። በዚህም መሠረታዊ አገልግሎቶቹን መልሰው ሥራ ለማስጀመር ለጥገና ወደ ትግራይ […]

ሩሲያ አሜሪካ በዩክሬኑ ጦርነት ቀጥተኛ ተሳታፊ ናት ስትል ከሰሰች፡፡

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 27፣ 2014 ሩሲያ አሜሪካ በዩክሬኑ ጦርነት ቀጥተኛ ተሳታፊ ናት ስትል ከሰሰች፡፡ ይህ የሞስኮ ወቀሳ የተሰማው የዩክሬን ወታደራዊ መረጃ ምክትል ሃላፊ ቫዲም ስኪቢትስኪ ከአሜሪካ የተበረከተላቸው የረዥም ርቀት የሮኬት ማስወንጨፊያ ስርዓቶች በጥሩ የሳተላይት ምስል እና እውነተኛ መረጃ አቀባይ መሆናቸውን ከገለፁ በኋላ ነው፡፡ ምክትል ሃላፊው ከቴሌግራፍ ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቆይታ ከጥቃቱ በፊት በአሜሪካ እና በዩክሬን […]

የናንሲ ፔሎሲ የታይዋን ጉብኝት እውን መሆኑን ተከትሎ የቻይና ከፍተኛ እርምጃ እየተጠበቀ ነው ተባለ፡፡

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 27፣ 2014 የናንሲ ፔሎሲ የታይዋን ጉብኝት እውን መሆኑን ተከትሎ የቻይና ከፍተኛ እርምጃ እየተጠበቀ ነው ተባለ፡፡ ያለፉት ጥቂት ቀናትን ቀልብ ስቦ የነበረው የአሜሪካ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ናንሲ ፔሎሲ የታየይዋን ጉብኝት ማክሰኞ ምሽት ይፋ መሆኑን ተከትሎ የቻይና የአስፈሪ እርምጃ ማስጠንቀቂያዎች በተከታታይ እንደሚሰሙ መገናኛ ብዙሃኑ እየዘገቡ ይገኛል፡፡፡ ቤጂንግ በአፈ-ጉባኤዋ ጉብኝት ብስጭቷን የገለፀች ሲሆን እንደ […]