loading
የተወካዮች ምክር ቤት አሸባሪው የሸኔ ቡድን በምዕራብ ወለጋ በንጹሀን ዜጎች ላይ ያደረሰውን አደጋ በፅኑ አወገዘ፡

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 28፣ 2014 የተወካዮች ምክር ቤት አሸባሪው የሸኔ ቡድን በምዕራብ ወለጋ በንጹሀን ዜጎች ላይ ያደረሰውን አደጋ በፅኑ አወገዘ፡፡ ምክር ቤቱ የሽብር ቡድኑ በጸጥታ ሀይሎች ጥቃት እየደረሰበት በመሆኑ ከጥቃቱ በመሸሽ በምዕራብ ወለጋ ንጹሀን ዜጎች ላይ አደጋ አድርሷል ብሏል። በኦሮሚያ ክልል፣ ቄለም ወለጋ ዞን የሚገኙ ንጹሀን ዜጎቻችን ላይ የፈጸመው ጭፍጨፋ በእጅጉ የሚወገዝ መሆኑን አስታውቋል፡፡ በዜጎቻችን […]

የመንግስት ህግ የማስከበር ሀላፊነት ጥያቄ ውስጥ መግባቱ አሳስቦኛል -ኢዜማ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 28፣ 2014 የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ ኢዜማ ፓርቲ መንግስት የህግ የበላይነትን የማስከበር ሃላፊነቱ ከዕለት ዕለት ጥያቄ ውስጥ እየገባ መምጣቱ በብርቱ አስግቶኛል አለ።ፓርቲው ይህን ያለው በቄለም ወለጋ በንጹሀን ዜጎች ላይ የደረሰውን አሰቃቂ ግድያ አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ ነው፡፡ ኢዜማ “በድንገት መጥቶ ህዝብን ከሚያጠቃው እኩይ አካል እኩል ዜጋውን የመጠበቅ ግዴታ ኖሮበት የማይጠብቀው መንግስት ተጠያቂ ነው” […]

የሱዳኑ ሉዓላዊ ምክር ቤት መሪ ጄኔራል አብዱል ፈታህ አልቡርሃን ጦር ሰራዊቱ ከመንግስት አስተዳዳሪነቱ እንደሚነሳ አስታወቁ፡፡

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 28፣ 2014 የሱዳኑ ሉዓላዊ ምክር ቤት መሪ ጄኔራል አብዱል ፈታህ አልቡርሃን ጦር ሰራዊቱ ከመንግስት አስተዳዳሪነቱ እንደሚነሳ አስታወቁ፡፡በመፈንቅለ መንግስት የመሪነቱን ስፍራ የያዙት አል ቡርሃን ጦሩ ከፖለቲካዊ ውይይቶች ራሱን እንደሚያግል ያስታወቁ ሲሆን የሲቪል የሽግግር መንግስት እንዲመሰርቱ እንደሚፈቅድ ገልፀዋል። የጄኔራሉ መግለጫ የተሰማው ካለፈው ሳምንት ጀምሮ ወታደራዊ አገዛዝ እንዲያበቃ የሚጠይቁ መጠነ ሰፊ ህዝባዊ ተቃውሞዎች መቀጠላቸውን ተከትሎ […]

በቀን ኮታ የተደለደለው የነዳጅ ስርጭት

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 29 ፣ 2014 የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ተሽከርካሪዎች በቀን መሙላት የሚችሉት የነዳጅ ኮታ ድልድል ይፋ ሆነ፡፡ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ተሽከርካሪዎችን ብቻ ተጠቃሚ የሚያደርገው አዲሱ የነዳጅ ድጎማ ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ መሆን ጀምሯል፡፡ በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ ተሽከርካሪዎች የታለመለት የነዳጅ ድጎማ ተጠቃሚ ለመሆን አስፈላጊ መረጃዎችን በመስጠት በኢትዮ ቴሌኮም የሽያጭ […]

ኢጋድ ኢትዮጵያ በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል የተከሰተውን ችግር በሰላማዊ አማራጭ ለመፍታት መወሰኗን አደነቀ፡፡

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 29 ፣ 2014 ኢጋድ ኢትዮጵያ በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል የተከሰተውን ችግር በሰላማዊ አማራጭ ለመፍታት መወሰኗን አደነቀ፡፡39ኛው የኢጋድ መሪዎች አስቸኳይ ጉባኤ በምስራቅ አፍሪካ ሰላምና ደህንነት፣ ኢኮኖሚያዊ ትብብር፣ አካባቢያዊና ሀገራዊ ፖለቲካዊ ለውጦች፣ እንዲሁም በሰው ሰራሽና ተፈጥሯዊ አደጋዎች ዙሪያ በኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ መክሯል። የአባል ሀገራቱ መሪዎች የኢትዮጵያ መንግስት ሀገራዊ ምክክር ለማድረግ ያሳየውን ቁርጠኝነትና በሰሜኑ […]

በጠቅላይ ሚኒስትራቸው እምነት ያጡ የእንግሊዝ ሚኒስትሮች ስራ መልቀቅ::

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 29 ፣ 2014 በእንግሊዝ በጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን እምነት አጣን በማለት የሥራ መልቀቂያ የሚያስገቡ ባልስልጣናት ተበራክተዋል ተባለ፡፡ በርካታ ሚኒስትሮች ከጆንሰን ጋር መስራት እደማይችሉ በመግለፅ ነው የሥራ መልቀቂያቸውን ያስገቡት ተብሏል፡፡ የአብዛኞቹ ምክንያት ተመሳሳይ ሲሆን በጠቅላይ ሚኒስትሩና አስተዳደራቸው ላይ ያላቸው እምነት ከእለት ወደ እለት እየተሸረሸረ መምጣቱ መሆኑን ዩሮ ኒውስ ዘግቧል፡፡ በትናንትናው እለት የሥራ […]

እንቦጭ ተመግቦ ሰውን የሚመግበው እንጉዳይ…

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 13፣ 2014 እንቦጭን በመመገብ ማጥፋት የሚችል የእንጉዳይ ዝርያ በምርምር መገኘቱን የኢትዮጵያ ደን ልማት አስታወቀ። በኢትዮጵያ ደን ልማት የደን ውጤቶች እና ኢኖቬሽን ዳይሬክተር አቶ ዳንኤል ገበየሁ እንቦጭ አረምን ለማጥፋት ብዙ ጥረትና ምርምር ሲደረግ መቆየቱን ገልጸው በአሁኑ ወቅት እንቦጭን በመመገብየሚያጠፋ እንጉዳይ ዝርያ በምርምር ተገኝቷል ብለዋል። በምርምሩ መሠረት እንቦጭ ያለበት ቦታ ላይ እንጉዳዩ እንዲዘራ ይደረጋል […]

አውስትራሊያ የኮቪድ-19 ስርጭት መስፋፋቱን ተከትሎ ቤት ሆኖ መስራትን እንደ አማራጭ እያጤነችው መሆኑ ተነገረ፡፡

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 13፣ 2014 አውስትራሊያ የኮቪድ-19 ስርጭት መስፋፋቱን ተከትሎ ቤት ሆኖ መስራትን እንደ አማራጭ እያጤነችው መሆኑ ተነገረ፡፡በኮቪድ-19 ምክንያት ሆስፒታል የሚገቡ ሰዎች ቁጥር ከፍ ማለቱን ተከትሎ የአውስትራሊያ ዜጎች ቤታቸው ውስጥ ሆነው እንዲሰሩ እና ጭምብል እንዲለብሱ ተጠይቀዋል። ሀገሪቱ በአዳዲስ የኦሚክሮን ተህዋሲ የሶስተኛ ዙር ማዕበል ውስጥ የምትገኝ ሲሆን በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ የተጠቂዎችን መጨመር ለመቋቋም የሁለተኛ ምዕራፍ […]