loading
የወባ በሽታን ከሀገሪቱ ለማጥፋት ህብረተሰቡ የወባ ማስወገድ አፈጻጸም መመሪያዎችንና መከላከያ ዘዴዎችን በአግባቡ ሊተገብር እንደሚገባ የጤና ሚኒስቴር አሳሰበ፡፡

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 18፣ 2014 የወባ በሽታን ከሀገሪቱ ለማጥፋት ህብረተሰቡ የወባ ማስወገድ አፈጻጸም መመሪያዎችንና መከላከያ ዘዴዎችን በአግባቡ ሊተገብር እንደሚገባ የጤና ሚኒስቴር አሳሰበ፡፡ የወባ ቀንን አስመልክቶ መግለጫ የሰጡት የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ደረጀ ድጉማ 75 በመቶ የሚሆነው የኢትዮጵያ መልክዐ ምድር ለወባ በሽታ ስርጭት አመቺ መሆኑን ጠቅሰዋል። 52 በመቶ የሚሆነው የሀገሪቱ ህዝብ በእነዚህ አካባቢዎች እንደሚኖር ተናግረዋል። በወባ […]

ሩሲያ ዩክሬን ላይ የኒውክሌር ግጭት ሊቀሰቀስ እንደሚችል አስጠነቀቀች::

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 18፣ 2014 ሩሲያ ዩክሬን ላይ የኒውክሌር ግጭት ሊቀሰቀስ እንደሚችል አስጠነቀቀች:: ሞስኮ ባወጣችው መግለጫ ኔቶ ለዩክሬን የጦር መሳሪያ በማቀበል የእጅ አዙር ጦርነት ከፍቶብኛል ስትል ወቀሳ ሰንዝራለች፡፡ የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቨሮቭ ከአንድ የሀገሪቱ ቴሌቪዥን ጣቢያ ጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅ መላው ዓለም ይህን ጉዳይ አቅልሎ መመልከት የለበትም ሲሉ አስጠንቅቀዋል፡፡ የላቭሮቭ ቃለ መጠይቅ የተሰራጨው […]

በንጹሃን ሕይወትና ንብረት ላይ የሚደርስን ጥፋት አንታገስም-የአማራ ክልል::

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 20 ፣ 2014 በጎንደር ከተማ በተቀሰቀሰ ግጭት በሰው ሕይወትና ንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን የአማራ ክልል አስታወቀ፡፡ ግጭቱ የተቀሰቀሰው ዕለተ ማክስኞ ሲሆን ክልሉ በሰጠው መግለጫ የጸቡ ምክንያት ሃይማኖታዊ ሽፋን ያለው መሆኑን አብራርቷል፡፡ ሼህ ከማል ለጋስ የተባሉ ግለሰብ ህይወት ማለፍን ተከትሎ የቀብር ስነ ስርዓት በሚፈጸምበት ወቅት በአቅራቢያው በሚገኝ ቤተ ክርስቲያን ለቀብር የሚሆን ድንጋይ […]

ለጋሽ አካላት በአፍሪካ ቀንድ ለምግብ እጥት ለተጋለጡ ወገኖች 1 ነጥብ 4 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ ቃል ገቡ፡፡

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 20 ፣ 2014 ለጋሽ አካላት በአፍሪካ ቀንድ ለምግብ እጥት ለተጋለጡ ወገኖች 1 ነጥብ 4 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ ቃል ገቡ፡፡ በአፍሪካ ቀንድ አካባቢ ከ40 ዓመታት በላይ ታይቶ የማያውቅ የድርቅ አደጋ መከሰቱን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ገልጿል፡፡ በዚህም የተነሳ ቁጥራቸው ከ15 ሚሊዮን የሚበልጥ ሰዎች ለከፋ የምግብ እጥረት አደጋ ተጋልጠዋል ነው የተባለው፡፡ […]

ትግራይ ዩኒቨርሲቲዎች ለተፈናቀሉ ተማሪዎች ዲግሪ እንደማይሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ::

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 20 ፣ 2014 ከትግራይ ዩኒቨርሲቲዎች ለተፈናቀሉ ተማሪዎች ዲግሪ እንደማይሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ:: ከትግራይ ክልል ዩኒቨርሲቲዎች ተፈናቅለው በአደራ በሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ተምረው ለተመረቁ ተማሪዎች፣ መደበኛ ዲግሪ ሚኒስቴሩ ለመስጠት እንደሚቸገር ገልጸዋል፡፡ በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች በትምህርት ሚኒስቴር ዋስትና ገብተው የተመረቁ ከትግራይ ዩኒቨርሲቲዎች የተፈናቀሉ ከ4ሺህ በላይ ተማሪዎች መደበኛ ዲግሪ ስለተከለከልን ሥራ ለመቀጠርና ለመወዳዳር አልቻልንም ሲሉ ለሪፖርተር ተደጋጋሚ […]

ደቡብ አፍሪካ ወደ አምስተኛው ዙር የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ማዕበል መግባቷ ተነገረ::

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 20 ፣ 2014 ደቡብ አፍሪካ ወደ አምስተኛው ዙር የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ማዕበል መግባቷ ተነገረ:: ደቡብ አፍሪካ ወደ አዲስ የኮቪድ- 19 ማዕበል እየገባች መሆኑን የሀገሪቱ የወረርሽኝ ምላሽ እና ፈጠራ ማዕከል አስታውቋል። የቤታ እና ኦሚክሮን ልውጥ ባህሪ ያላቸውን ቫይረሶችን በመለየት ዝነኛ የሆነው የጥናት ማዕከል ሃላፊ አምስተኛው ዙር የወረርሽኝ ስርጭት መከሰቱን በትዊተር ገፁ ላይ ይፋ […]