ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ በጦር ግንባር ጀብድ ፈፅመው ድል ላመጡ ሴቶች ምስጋና አቀረቡ::
አዲስ አበባ፣ የካቲት 29፣ 2014 ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን በተለያዩ ዝግጅቶች በመከላከያ መኮንኖች ክበብ ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ በተገኙበት ተከብሯል። ፕሬዚዳንቷ በዚህ ወቅት ሴት የመከላከያ ሰራዊት አባላት በናንተ ድርብ መስዋዕትነት ሀገር ትቀጥላለችና ለናንተ ክብር መስጠት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡ የሀገራችን ሰላም በሴቶች ተጋድሎ ይረጋገጣል፤ በጀግና ሴቶች ሰማዕትነት ሀገራችን ታፍራ እና ተከብራ ትኖራለችም ብለዋል፡፡ አሸባሪው የህወሓት ቡድን በኢትዮጵያ ላይ […]