loading
የሠራዊቱን ስም ማጠልሸት በሀገር ላይ አደጋ ለመጣል መሞከር ነው-ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ

አዲስ አበባ፣ ጥር 4፣ 2014 የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ሠራዊቱ ላይ አሉባልታ የሚነዙ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ አስጠነቀቁ፡፡ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የአገር መከላከያ ሠራዊት ከሌሎች የጸጥታ አከላት ጋር በመቀናጀት በኢትዮጵያ ላይ ተደቅኖ የነበረውን የህልውና አደጋ በመቀልበስ አኩሪ ገድል መፈጸሙን ተናግረዋል፡፡ ሠራዊቱ የሁሉም ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች አብራክ ክፋይና የኢትዮጵያ ሉዓላዊነት የመጨረሻው […]

የከተማ አስተዳደሩ ባለፉት አመታት ከቤቶች ግንባታ ጋር በተያያዘ የ54 ቢሊዮን ብር እዳ የመክፈል ፈተና እንደገጠመው ተገለጸ፡፡

አዲስ አበባ፣ ጥር 4፣ 2014 የከተማ አስተዳደሩ ባለፉት አመታት ከቤቶች ግንባታ ጋር በተያያዘ የ54 ቢሊዮን ብር እዳ የመክፈል ፈተና እንደገጠመው ተገለጸ፡፡ይህ የተገለጸው የአዲስ አበባ ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በስምንት ቢሊዮን ብር በጀት የአምስት ሺህ የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ግንባታ ባስጀመሩበት ወቅት ነው።ይህ የተጀመረው የቤቶች ፕሮጀክት በተገጣጣሚ ቴክኖሎጂ የሚሰራና በአጭር ጊዜ ተገንብቶ የሚጠናቀቅ ነው ተብሏል። ከንቲባዋ በፕሮግራሙ […]

በደቡብ አፍሪካ ፓርላማ ቃጠሎ ተጠርጥሮ በሽብር ወንጀል የተከሰሰው የጎዳና ተዳዳሪ

አዲስ አበባ፣ ጥር 4፣ 2014 ከደቡብ አፍሪካ ፓርላማ ቃጠሎ ጋር በተያያዘ የተጠረጠረው ግለሰብ ሽብርተኝነትን ጨምሮ ከ6 በላይ ክስ ተመሰረተበት፡፡ ትናንትና ለሁለተኛ ጊዜ ችሎት የቀረበው የ49 ዓመቱ የጎዳና ተዳዳሪ ዜንዳይል ክሪስርማስ ማፊ ከሽብርተኝነት በተጨማሪ በዘረፋና ከባድ የእሳት ቃጠሎ በማስነሳት ወንጀሎች መከሰሱም ተሰምቷል፡፡ የአቃቤ ህግ ቃል አቀባይ ኤሪክ ንታባዛሊላ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ አቃቤ ህግ በተጠርጣሪው ላይ ተጨማሪ […]