loading
የኢትዮጵያን ስም የሚያጠለሸው አዋጅ ውድቅ ተደረገ::

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 07፣ 2014 ኢትዮጵያን በዘር ተኮር ጭፍጨፋ ለመጠየቅ ታስቦ የነበረው ህግ መሰረዙ ይፋ ተደረገ፡፡ የኢትዮጵያ አሜሪካውያን የዜጎች ምክር ቤት ከከፍተኛ የአሜሪካ ባለስልጣናት ጋር ያደረገውን ስብሰባ መሰረት በማድረግ ሴናተር ጂም ኢንሆፍ ለምክር ቤቱ መረጃ መላኩ ታውቋል፡፡ በመረጃውም በኢትዮጵያ “የዘር ተኮር ጭፍጨፋ ተካሂዷል” በሚል ሀሰተኛ ውንጀላ ኢትዮጵያን ለመጠየቅ የሚረዳና በአሜሪካ ሴኔት ቢሮ የታሰበው ሕግ ማለትም […]

አራት የፖሊስ አባላት ወድቆ ያገኙትን 3 ሺህ 900 ዶላር አስረከቡ::

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 07፣ 2014 አራት የአዲስ አበባ ፖሊስ አባላት አባላት ወድቆ ያገኙትን 3 ሺህ 900 ዶላር ማስረከባችው ተገለጸ፡፡ በታማኝነት እና በቅንነት ማገልገል ከሕዝብ እና ከመንግሥት የተሰጠን አደራ ነው ያሉት አራቱ የአዲስ አበባ ፖሊስ አባላት ወድቆ ያገኙትን 3 ሺሕ 900 የአሜሪካ ዶላር ማስረከባቸውን ፖሊስ አስታውቋል።ምክትል ኢንስፔክተር ዘነበ እሸቱ፣ ምክትል ኢንስፔክተር ዳግም ግርማ እና ዋና ሳጅን […]

በአዲስ አበባ የሚገኙ ባለኮከብ ሆቴሎች ለዳያስፖራዎች እስከ 30 በመቶ ቅናሽ አደረጉ::

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 07፣ 2014 በአዲስ አበባ የሚገኙ ባለ ኮከብ ሆቴሎች ለገናና ጥምቀት በዓላት ወደ ኢትዮጵያ ለሚመጡ አንድ ሚሊዮን ዲያስፖራዎች እስከ ሰላሳ በመቶ የሚደርስ ልዩ ቅናሽ ማድረጋቸውን የአዲስ አበባ ሆቴል ባለቤቶች ማህበር ገለጸ። የአዲስ አበባ የሆቴል ባለቤቶች ማህበር ሥራ አስኪያጅ አቶ አምሀ በቀለ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅትእንደገለጹት፤ በመዲናዋ የሚገኙ ባለኮከብ ሆቴሎች ለገናና ለጥምቀት በዓላት ወደ ኢትዮጵያ […]

ጥይት ያለአግባብ አታባክኑ-ዶክተር ይልቃል ከፋለ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 13፣ 2014 ሁሉም ለቀጣይ ትግል በሚዘጋጅበት ወቅት ጥይት ያለ አግባብ ማባከን አይገባም ሲሉ የአማራ ክልልርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ አሳሰቡ፡፡ርዕሰ መስተዳድሩ በሰጡት መግለጫ ከአሸባሪው የትሕነግ ወራሪ ቡድን ጋር በተካሄደው ፍልሚያበጀግንነት ተጋድሎ ያደረጉ የጸጥታ አካላት ለከፈሉት መስዋእትነት ትልቅ ክብር አለን ብለዋል። በግንባር ለተፋለሙ ጀግኖች አቀባበል ማድረግ ተገቢ ቢሆንም ለአቀባበል በሚል የጥይት ተኩስማድረግ ማኅበረሰቡን […]

ለ12 ሰዓታት ዋኝተው ህይዎታቸውን ከአደጋ ያዳኑት የፖሊስ ሚኒስትር

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 13፣ 2014 ሄሊኮፕተራቸው ባህር ላይ የወደቀችባቸው የማዳጋስካር የፖሊስ ሚኒትስር ለ12 ሰዓታት ያህል ዋኝተውራሳቸውን ማዳናቸው ተሰማ፡፡ ሚኒስትሩ ሰርጌ ጌሌ ከሄሊኮፕር አደጋው በህይወት ከተረፉት ሁለት ሰዎች መካከል እንዱ ናቸውተብሏል፡ ዩሮ ኒውስ እንደዘገበው የ57 ዓመቱ ጌሌ ለ12 ሰዓታት ያህል ከዋኙ በኋላ ማሃምቦ በተባለች የባህርዳርቻ አቅራቢያ የሚገኙ ነዋሪዎችና ዓሣ አጥማጆች አግኝተዋቸው ወደ ህክምና ወስደዋቸው ነውበህይወት የተረፉት፡፡ […]

ውድ የኢትዮጵያ ልጆች አድሏዊውን ዓለም እርቃኑን አስቀርታችሁታል-አቶ ደመቀ መኮንን

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 20፣ 2014 መንግስት ያቀረበውን ወደ ሀገር ቤት ጥሪ ተቀብለው ለገቡ ኢትዮጵያዊያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች የአቀባበል መርሃግብር ተካሄደ፡፡በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ለእንግዶቹ እንኳን ወደ እናት ሀገራችሁ በሰላም መጣችሁ የሚል መልእክት አስተላልፈዋል፡፡አቶ ደመቀ በእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግራቸው በተለያዩ ክፍለ ዓለማት የምትኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ኖ […]

አሁንም ትኩረት የሚያሻው የኮቪድ-19 ስርጭት

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 20፣ 2014 ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ የላቦራቶሪ ናሙና ምርመራ ከ5 ሺህ በላይ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን ጤና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ ሚኒስቴሩ በመግለጫው እንዳለው ምርመራ ከተደረገላቸው 13 ሺህ 280 ሰዎች መካከል 5 ሺህ 185 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።ይህም እስካሁን በአጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን ቁጥር 405 ሺህ 745 ከፍ እንዳደረገው ነው ሚኒስቴሩ የገለጸው፡፡ በሌላ […]

ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን በአፍሪካ ሀገራት ላይ ጥለውት የነበረውን የጉዞ ክልከላ ማንሳታቸው ተሰማ፡፡

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 20፣ 2014 ባይደን በይፋ እንደተናገሩት የኮቪድ-19 ክትባት የወሰዱ ሰዎች በኦሚክሮን ቫይረስ ቢያዙ እንኳ ለከፋጉዳት እንደማይዳረጉ የህክምና ባለ ሙያዎች አረጋግጠውልኛል ብለዋል፡፡ በመሆኑም በደቡባዊ አፍሪካ ከሚገኙ ስምንት ሀገራት የሚመጡ ተጓዦች ወደ አሜሪካ እንዳይገቡጥለነው የነበረው እገዳ ከእግዲህ አይሰራም ተጓዦቹ መከተባቸው በቂ ነው ብለዋል፡፡ዋሽንግተን የጉዞ ክልከላ ጥላባቸው የነበሩት ሀገራት ደቡብ አፍሪካ፣ ቦትስዋና፣ ዚምባቡዌ፣ ናሚቢያ፣ሌሴቶ፣ ኢስዋቲኒ፣ ሞዛምቢክና […]

2 ሺህ 921 የጤና ተቋማት ወድመዋል-የጤና ሚኒስቴር

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 21፣ 2014 በአሸባሪውቹ ህወሃት እና ሸኔ በአራት ክልሎች 2 ሺህ 921 የጤና ተቋማት መውደማቸውን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ደረጀ ዱጎማ ለፋና እንደተናገሩት በአማራ፣ አፋር ፣ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች እና ኦሮሚያ ክልል የተወሰኑ አካባቢዎች በሽብር ቡድኖቹ የጥፋት እጆች የጤናው ሴክተር ቀዳሚ ውድመት ደርሶበታል ብለዋል። በአማራ ክልል 40 ሆስፒታሎች፣ 450 ጤና ጣቢያዎች […]

በአንድ ሳምንት ከ6 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተያዙ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 21፣ 2014 በአንድ ሳምንት ውስጥ ክብረ ወሰን የሆነ የኮቪድ-19 ታማሚዎች ቁጥር ተመዘገበ ከዲሴምበር 22 እስከ 28 ባለው ጊዜ በየቀኑ በአማካይ 935 ሺህ ገደማ ሰዎች በቫይረሱ ይያዙ እንደነበር አልጀዚራ በዘገባው አስነብቧል፡፡ በዓለማቸው በአንድ ሳምንት ውስጥ ብቻ ከ6 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሲሆን ይህም በሽታው ከተከሰተ ወዲህ ትልቁ ቁጥር ነው ተብሏል፡፡ መረጃዎች […]