ታላቁን የድል ዜና መቀሌ ላይ ሆነን እናበስራለን- ሌ/ጄ ባጫ ደበሌ
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 1፣ 2014 የመከላከያ ሠራዊት ግንባታ ሥራዎች ዋና አስተባባሪ ሌተናል ጄኔራል ባጫ ደበሌ የሕወሓት ሽብር ቡድንን እስከ መጨረሻው በመቅበር ታላቁን የድል ዜና መቀሌ ላይ ሆነን እናበስራለን አሉ። የልዩ ዘመቻዎች ኃይል፣ የሪፐብሊክ ጥበቃ ኃይል እና የአየር ወለድ አባላት በጭንቅ ላይ ያለች አገርን ችግር የፈቱ የጭንቅ ቀን ደራሾች መሆናቸውን አስታውቀዋል። ሌተናል ጄኔራሉ ይህንን የተናገሩት የመጀመሪያው […]