አሸባሪውን የሕወሓትን ኃይል ከታሪክ ገጽ ለመደምሰስ ጊዜው አሁን ነዉ -የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት
አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 4፣ 2013 ሀገር በመከላከል ዘመቻው ለመሳተፍ እድሜያችሁና ዐቅማችሁ የሚፈቅድላችሁ ኢትዮጵያውያን ሁሉ የመከላከያ ሠራዊቱን እንዲቀላቀል ጥሪ ቀረበ፡፡ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ባደረገዉ ጥሪ ፣ዐቅማችሁ የሚፈቅድላችሁ ኢትዮጵያውያን ሁሉ የመከላከያ ሠራዊቱን ልዩ ኃይሉንና ሚሊሻውን በመቀላቀል የሀገር ዘብነታችሁን የምታሳዩበት ትክክለኛው ጊዜ አሁን ነው ብሏል፡፡ አሸባሪውን የሕወሓት ኃይል ከታሪክ ገጽ ለመደምሰስ የሀገር መከላከያ ሠራዊታችን፣ የክልል ልዩ ኃይሎችና ሚሊሻዎች፣ […]