loading
ለሕዳሴ ግድብ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ-ግብር በሙኒክ ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 19፣ 2013 ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ-ግብር በሙኒክ ተካሄደ፡፡ በጀርመን ሙኒክ በኢትዮጵያ ማህበረሰብ አዘጋጅነት በተዘጋጀው በዚህ ፕሮግራም ላይ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ተሳትፈዋል። በተለያዩ ዘርፎች ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር “ደግሞ ለዓባይ” በሚል መሪ ቃል ተካሂዷል። በፕሮግራሙ ላይ ኢትዮጵያዊያኑ እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያኑ ለታላቁ ሕዳሴ ግድብ በቦንድ […]

የቱኒዚያው ፕሬዚዳንት ካይስ ሰይድ የሀገሪቱን ፓርላማ በተኑ፡፡

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 19፣ 2013 የቱኒዚያው ፕሬዚዳንት ካይስ ሰይድ የሀገሪቱን ፓርላማ በተኑ፡፡ ፕሬዚዳንቱ የቱኒዚያዉን ጠቅላይ ሚኒስትሩንም ከስልጣናቸ አባረዋል፡፡ የፕሬዚዳንቱ ተግባር መፈንቅለ መንግስት ነው ሲሉ ተቃዋሚዎች ገልጸውታል፡፡ ሮይተርስ እንደዘገበዉ ፕሬዚዳንቱ በኮቪድ-19 ሳቢያ በሀገሪቱ የተከሰተውን አመጽ ተከትሎ ነው እርምጃውን የወሰዱት ተብሏል፡፡ በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩ ቱኒዚያዊያን የሀገሪቱ መንግስት ኮቪድ -19ን የያዘበት መንገድ አግባብ አይደለም በሚል ለተቃውሞ ወጥተዉ ነበር፡፡ በከተማዋ ቱኒዝ እና በሌሎች ከተሞችም ለተቃውሞ […]

6 ሰዓታትን የፈጀ ስኬታማ ቀዶ ህክምና-በኢትዮጵያ

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 19፣ 2013 የልብ የደም ስር ነቅሎ መትከል እና የልብ በር ቀዶ ህክምና ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጵያ መካሄዱን የጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ሐኪም ገለጹ፡፡ ቀዶ ህክምናው 6 ሰዓታትን የፈጀ መሆኑም ተገልጿል፡፡ ቀዶ ህክምናውን ለየት የሚያደርገው የልብ የደም ስር ነቅሎ መትከል እና የልብን በር ቀዶ ህክምና በአንድ ላይ መደረጉ መሆኑን በጥቁር አንበሳ የልብ ማዕከል የልብ […]

ፕሮፌሰር አንቶኒ ፋውቺ አሜሪካ ኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከል የምትሄድበት መንገድ ስህተት ነው አሉ፡፡

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 19፣ 2013  ፕሮፌሰር አንቶኒ ፋውቺ አሜሪካ ኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከል የምትሄድበት መንገድ ስህተት ነው አሉ፡፡ ፕሮፌሰሩ ከሲ ኤን ኤን ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ በመላው አሜሪካ በርካታ በቀላሉ ለቫይረሱ ተጋላጭ የሆኑ ሰዎች አሁንም ክትባት አላገኙም ብለዋል፡፡ ይሄ ደግሞ የበሽታውን ስርጭት ለማሰፋት ዋነኛ መንስኤ ይሆናል ነው ያሉት ፕሮፌሰር ፋውቺ፡፡ አዲሱን የቫይረስ ዝርያ ስርጭት የሥርጭት […]

ጣሊያን የገጠማትን ሰደድ እሳት ለመቋቋም ድጋፍ ጠየቀች::

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 19፣ 2013 ጣሊያን የገጠማትን ሰደድ እሳት ለመቋቋም የአውሮፓ ህብረትን ድጋፍ ጠየቀች፡፡ የሀገሪቱ ባለስልጣናት ከአሁን ቀደም ታይቶ የማይታወቅ ብለው የጠሩት የእሳት አደጋ በአስር ሺዎች ሄክታር የሚለካ መሬት መሸፈኑ ተነግሯል፡፡ የእሳት አደጋው የደረሰው ሳርዲኒያ በተባለች ደሴት ሲሆን በርካታ የደሴቷ ነዋሪዎች ራሳቸውን ከአደጋው ለማዳን መኖሪያ አካባቢዎቻቸውን ለቀው ወጥተዋል፡፡ ፈረንሳይና ግሪክ የጣሊያን መንግስት ያቀረበውን የድጋፍ […]