እስካሁን የምርጫ ውጤት ተጠቃልሎ አልደረሰኝም-ምርጫ ቦርድ
አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 25፣ 2013 በተለያዩ ምክንያቶች እስካሁን የሁሉንም ምርጫ ክልሎች ውጤት ይፋ ማድረግ አለመቻሉን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ገለጸ። እስካሁን ባለው ሂደት ምርጫ ከተካሄደባቸው የምርጫ ክልሎች የ26ቱ ውጤት አለመድረሱን ቦርዱ አስታውቋል። የቦርዱ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ ፤ በድምር መዘግየት፣ በትራንስፖርት ችግር እንዲሁም የፖለቲካ ፓርቲዎች አቤቱታ ምክንያት የምርጫ ክልሎች ውጤት ወደ ማዕከል ተጠቃሎ አልደረሰም ብለዋል። […]