ዜጎች በምርጫ የሚሳተፉባቸው አማራጭ መንገዶች
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 19 ፣ 2013 በምርጫ ወቅት ዜጎች በንቃት የሚሳተፉባቸው በርካታ አማራጭ መንገዶች መኖራቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ገለጹ፡፡ በሀገራችን ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት እንዲወለድ የዜጎች ንቁ ተሳትፎ እጅግ ወሳኝ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንንም በተግባር ሊያረጋግጡ ይገባል ብለዋል፡፡ ዜጎች በምርጫ ወቅት ተሳትፎአቸውን ከሚያረጋግጡባቸው መነገዶች አንዱ ካርድ ወስደው በሰላማዊ መንገድ የሚሆናቸውን ለመምረጥ ራስን ከማዘጋጀት ይጀምራል ነው […]