loading
በዐቢይ ፆም ወቅት ሰላም፣ ፍቅር፣ ይቅር ባይነት መታዘዝና አካፍሎ መብላትን መተግበር እንደሚገባ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ገለፁ፡፡

አዲስ አበባ፣የካቲት 29፣ 2013 በዐቢይ ፆም ወቅት ሰላም፣ ፍቅር፣ ይቅር ባይነት መታዘዝና አካፍሎ መብላትን መተግበር እንደሚገባ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ገለፁ፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በዐቢይ ፆም ወቅት ሰላም፣ ፍቅር፣ ስምምነት፣ ይቅር ባይነት መታዘዝና አካፍሎ መብላትን ምዕመኑ መተግበር እንደሚገባው ጥሪ አቅርበዋል፡፡ ፓትርያርኩ የዐቢይ ጾም መግባትን ምክንያት በማድረግ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ በመግለጫቸውም […]

ለሴቶች ከፍ ያለ ደረጃ መድረስ ከትምህርት ሌላ ምንም መሰላል እንደሌለ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ገለጹ ፡፡

አዲስ አበባ፣የካቲት 29፣ 2013 ለሴቶች ከፍ ያለ ደረጃ መድረስ ከትምህርት ሌላ ምንም መሰላል እንደሌለ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ገለጹ ፡፡ ሴቶች በትምህርታቸው ውጤታማ በመሆን ከፍተኛ የሃላፊነት ቦታዎችን በብቃት መምራት እንደሚችሉ አምነው እንዲማሩ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ መክረዋል።ፕሬዚዳንቷ  ዓለም አቀፉን የሴቶች ቀን ምክንያት በማድረግ የቱሉ ዲምቱ ሁለተኛና መሰናዶ ትምህርት ቤትን ጎብኝተዋል። በጉብኝታቸው ከትምህርት ቤቱ የስርዓተ ጾታ ክበብ አባላት ጋር […]

በህዳሴው ግድብ ግንባታና የውሃ አሞላል ሂደት ዙሪያ በትብብር ለመስራት ያሉ ፈተናዎችና መልካም አጋጣሚዎች ላይ ያተኮረ ውይይት ተካሄደ ፡፡

አዲስ አበባ፣የካቲት 29፣ 2013 በህዳሴው ግድብ ግንባታና የውሃ አሞላል ሂደት ዙሪያ በትብብር ለመስራት ያሉ ፈተናዎችና መልካም አጋጣሚዎች ላይ ያተኮረ ውይይት ተካሄደ ፡፡ የውይይቱ ዓላማ በግድቡ ዙሪያ በእውነታ ላይ የተመሰረተና ትክክለኛ መረጃን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ማስተላለፍ ነው ተብሏል፡፡ ውይይቱ በዌብናር የተካሄ ሲሆን በውይይተቱ ከተሳተፉት መካከል በሀገር ውስጥና በአሜሪካን ሀገር የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን እንዲሁም አሜሪካዊያን ይገኙበታል፡፡ ተወያዮቹ በዋናነት […]

በኢኳቶሪያል ጊኒ በአንድ ወታደራዊ ካምፕ በደረሰ ፍንዳታ 20 ሰዎች ሲሞቱ በርካታ ሰዎች ቆስለዋል፡፡

አዲስ አበባ፣የካቲት 29፣ 2013 በኢኳቶሪያል ጊኒ በአንድ ወታደራዊ ካምፕ በደረሰ ፍንዳታ 20 ሰዎች ሲሞቱ በርካታ ሰዎች ቆስለዋል፡፡ በወታደራዊ ካምፑ ላይ አራት ከፍተኛ ፍንዳታዎች መድረሳቸው የታወቀ ሲሆን ከሞቱት 20 ሰዎች በተጨማሪ 600 የሚሆኑት ደግሞ መቁሰላቸው ተሰምቷል፡፡ ፍንዳታው የደረሰው የኢኮኖሚ ከተማ በሆነችው ባታ ከተማ አቅራቢያ በሚገኘው ንኮማ ንቶማ ወታደራዊ ካምፕ ነው፡፡ የፍንዳታው መንስኤ በአካባቢው የሚገኙ አርሶ አደሮች […]