በሱዳን በተለያዩ ከተሞች በኑሮ ውድነት ሳቢያ አዲስ ተቃውሞ መቀስሰቀሱ ተሰማ::
አዲስ አበባ፣የካቲት 3፣ 2013 በሱዳን በተለያዩ ከተሞች በኑሮ ውድነት ሳቢያ አዲስ ተቃውሞ መቀስሰቀሱ ተሰማ:: ተቃውሞው የተቀሰቀሰው በዳርፉር ግዛት በሚገኙ ከተሞች ሲሆን በሰልፉ የተሳተፉት በአብዛኛው ወጣቶች መሆናቸው ነው የተገለፀው፡፡ አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ እንደዘገበው ተቃዋሚ ሰልፈኞቹ በኑሮ ውድነት ሳቢያ ለርሃብ መጋለጣቸውን የሚገልፁ ጥያቄዎችን ይዘው ነው ጎዳና የወጡት፡፡ በደቡብ ዳርፉር ግዛት ዋና ከተማ ኒያላ ለተቃውሞ የወጡት ወጣቶች ሊበትኗቸው […]