loading
በመላዉ ዓለም የኮቪድ 19 ክትባት መሰጠት መጀመሩ ኢትዮጵያን ከቫይረሱ እንዳይጠነቀቁ ሊያደርግ አይገባም::

አዲስ አበባ፣ጥር 03፣ 2013 በመላዉ ዓለም የኮቪድ 19 ክትባት መሰጠት መጀመሩ ኢትዮጵያን ከቫይረሱ እንዳይጠነቀቁ ሊያደርግ አይገባም ሲሉ አርትስ ያነጋገራቸዉ በሚሊኒየም የኮቪድ 19 ኬር ሴንተር የነርስኒግ ዳይሬክተር ሲስተር ንጋት ወ/ማርያም አሳሰቡ ፡፡ በማዕከሉ ቀደም ሲል ከነበረዉ የታማሚዎች ቁጥርና የፅኑ ህክምና  የሚያስፈልጋቸዉ ሰዎች ቁጥር መበራከታቸዉን ያስታወሱት ሲስተር ንጋት ፤የኮቪድ 19 ክትባት ቢገኝም ለአፍሪካ ብሎም ለኢትዮጵያ ተዳራሽ የመሆኑ […]

ኬንያ እና ሶማሊያ አሁንም በመልካም ጉርብትናቸው የሚቀጡሉበት መንገድ አልተዘጋም ተባለ::

አዲስ አበባ፣ጥር 03፣ 2013 ኬንያ እና ሶማሊያ አሁንም በመልካም ጉርብትናቸው የሚቀጡሉበት መንገድ አልተዘጋም ተባለ:: ሶማሊያ ባለፈው ዲሴምበር ወር በውስጥ ጉዳዬ ጣልቃ ገባችብኝ በሚል መነሻ ከኬንያ ጋር የዲፕሎማሲ ግንኙነቷን በይፋ አቋርጣለች፡፡ ሁለቱ ሀገራት ግንኙነታቸው ወደ ነበረበት እንዲመለስ ተደጋጋሚ ጥረት ሲያደርጉ የአፍሪካ ህብረትም ውዝግቡ በሰላም እንዲፈታ አሳስቦ ነበር፡፡ ሶማሊያ ውስጥ በአስር ሽዎች የሚቆጠሩ ኬንያዊያን ሰራተኞች እንዳሉና በኬንያም […]

በዘንድሮ ሀገራዊ ምርጫ ለሚሳተፉ በጎ ፈቃደኞች ስልጠና እየተሰጠ ነው ::

አዲስ አበባ፣ጥር 04፣ 2013 በዘንድሮ ሀገራዊ ምርጫ ለሚሳተፉ በጎ ፈቃደኞች ስልጠና እየተሰጠ ነው ::የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ከዩ ኤን የልማት ፕሮግራም ጋር በመተባበር ነው በዘንድሮ ሀገራዊ ምርጫ ለሚሳተፉ በጎ ፈቃደኞች ስልጠና የሚሰጠው፡፡ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ስልጠናው በምርጫው ላይ በተለያዩ ዘርፎች የሚሳተፉ በጎ ፈቃደኞችን አቅም ለማሳደግ አንደሚረዳ ተናግረዋል። ለበጎ ፈቃደኞቹ ክፍተት ባለበት […]

የሃይሌ ማናስ አካዳሚ የ2ኛ ደረጃ አዳሪ ት/ቤት የመጀመሪያ ተማሪዎቹን ተቀበለ::

አዲስ አበባ፣ጥር 04፣ 2013 የሃይሌ ማናስ አካዳሚ የ2ኛ ደረጃ አዳሪ ት/ቤት የመጀመሪያ ተማሪዎቹን ተቀበለ:: የሃይሌ- ማናስ አካዳሚ ውጤት የሆነው ይህ አዲስ ጥራቱን የጠበቀ 2ኛ ደረጃ አዳሪ ት/ቤት በደብረ ብርሃን ተገንብቶ አገልግሎት መስጠት የጀመረ ሲሆን ለመጀመሪያ ጊዜ የ9ኛ ክፍል ተማሪዎቹን ተቀብሏል፡፡ በአዲሱ ካምፓስ ወላጆች በአካል ተገኝተው ልጆቻቸውን ያስመዘገቡ ሲሆን የጉብኝት እና የኮቪድ-19 የጥንቃቄ መመሪያ ገለፃ ላይ […]

ደቡብ አፍሪካ እስከመጪው ወር አጋማሽ ድረስ 20 የሚሆኑ የድንበር ኬላዎቿን ለመዝጋት ወሰነች::

አዲስ አበባ፣ጥር 04፣ 2013 ደቡብ አፍሪካ እስከመጪው ወር አጋማሽ ድረስ 20 የሚሆኑ የድንበር ኬላዎቿን ለመዝጋት ወሰነች:: ደቡብ አፍሪካ እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰችው በፍጥነት እየተስፋፋ የመጣው የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ክፉኛ ስላሳሰባት ነው፡፡ ድንበሮቹ ዝግ ሆነው በሚቆይበት ወቅትም ወደ ሀገሪቱ የሚገቡም ሆኑ ወደ ውጭ የሚወጡ ተጓዦች አይኖሩም ነው የተባለው፡፡ ከዚህ ጎን ለጎን የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት ለ20 ሚሊዮን ሰዎች […]

በሰሜን ምዕራብ ናይጄሪያ ጂሃዲስቶች ባደረሱት ጥቃት 13 ወታሮች ተገደሉ::

አዲስ አበባ፣ጥር 04፣ 2013 በሰሜን ምዕራብ ናይጄሪያ ጂሃዲስቶች ባደረሱት ጥቃት 13 ወታሮች ተገደሉ:: በዮቤ ግዛት በምትገኝ አንዲት መንደር አቅርቢያ በሚጓዙ ወታደራዊ ተሸከርካሪዎች ላይ በድንገት በተከፈተ ጥቃት ነው ወታደሮቹ የተገደሉት ተብሏል፡፡ አፍሪካ ኒውስ ወታደራዊ ምንጮችን ጠቅሶ እንደዘገበው የደፈጣ ተዋጊዎቹ በከባድ መሳሪያዎችና በሮኬት በሚወነጨፉ የእጅ ቦንቦች ጭምር ነው ጥቃቱን ያደረሱት፡፡ ወታደሮቹ ጥቃቱ ከተፈፀመበት 20 ኪሎሜትር ርቀት ላይ […]

ማላዊ በቮሮናቫይረስ ሳቢያ ሁለት የካቢኔ ሚኒስትሮቿን ማጣቷ በሀገሪቱ ትልቅ ሀዘን ፈጥሯል፡፡

አዲስ አበባ፣ጥር 05፣ 2013 ማላዊ በቮሮናቫይረስ ሳቢያ ሁለት የካቢኔ ሚኒስትሮቿን ማጣቷ በሀገሪቱ ትልቅ ሀዘን ፈጥሯል፡፡ የማላዊ ፕሬዳንት ላዛረስ ቺኩየራ የሚንስትሮቹን ሞት አስመልክተው ባደረጉት ንግግር የማይሰላ ኪሳራ ደርሶብናል ካሉ በኋላ በሀገሪቱ የሶስት ቀን ሀዘን መታወጁን ይፋ አድርገዋል በኮሮናቫይረስ መያዛቸው ከተረጋገጠ በኋላ ህይዎታቸው ያለፈው የትራንስፖርት ሚስትሩ ሲዲክ ሚያ እና የአካባቢ አስተዳደር ሚንስትሩ ሊንግሰን ብሬካኒያማ ናቸው፡፡ አልጀዚራ እንደዘገበው […]

ዩዌሬ ሙሴቬኒ የምርጫው ቀን ከመድረሱ በፊት የማህበራዊ ትስስር ገፆችን እንዲዘጉ አዘዙ፡፡

አዲስ አበባ፣ጥር 05፣ 2013 ዩዌሬ ሙሴቬኒ የምርጫው ቀን ከመድረሱ በፊት የማህበራዊ ትስስር ገፆችን እንዲዘጉ አዘዙ፡፡ ዩጋንዳ ጃኑዋሪ 14 ለምታካሂደው ምርጫ የተሳሳተ መረጃን በማሰራጨት ሁከት እንዲቀሰቀስ ያደርጋል በሚል ስጋት ከምርጫው ቀን አስቀድሞ ላሉት ሁለት ቀናት የበይነ መረብ አገልግሎት ዝግ ተደርጓል፡፡ አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ እንደዘገበው የሀገሪቱ የኮምኒኬሽን ቁጥጥር ባለስልጣናትም የሙሴቬኒን ትእዛዝ ተቀብለው የበይነ መረብ አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማትን […]

የደቡብ ክልል ፖሊስ ኮሌጅ ከ600 በላይ የልዩ ሀይል ፖሊሶችን እያስመረቀ ነው::

አዲስ አበባ፣ጥር 06፣ 2013 የደቡብ ክልል ፖሊስ ኮሌጅ ከ600 በላይ የልዩ ሀይል ፖሊሶችን እያስመረቀ ነው:: የደቡብ ክልል ፖሊስ ኮሌጅ በዛሬው እለት ከ600 በላይ የልዩ ሀይል ፖሊሶችን እያስመረቀ ነው፡፡ የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እርስቱ ይርዳ የደቡብ ፖሊስ ኮሌጅን ጎብኝተዋል፡፡ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ እና በእርሳቸው የተመራው ልዑክ የኮሌጁን ልዩ ልዩ የስራ ክፍሎች ተዘዋውሮ ጎብኝቷል፡፡

የአርባምንጭ ከተማ የጤና መሰረተ ልማት ላይ ያለዉን የአገልግሎት ጥራት ችግር ለማቅለል በትኩረት ሊሰራ ይገባል ተባለ ፡፡

አዲስ አበባ፣ጥር 12፣ 2013  የአርባምንጭ ከተማ የጤና መሰረተ ልማት ላይ ያለዉን የአገልግሎት ጥራት ችግር ለማቅለል በትኩረት ሊሰራ ይገባል ተባለ ፡፡በከተማዋ 3 የጤና ጣቢያዎችና 1 አጠቃላይ ሆስፒታል ያለ ሲሆን ከፍተኛ ህክምና የሚሹ የከተማ ነዋሪዎች በከተማዋ አገልግሎት ማግኘት እንዲችሉ ሆስፒታሎችን ማስፋት ላይ በትኩረት እተሰራ እንደሆነ አርትስ ያነጋገራቸዉ የከተማ ጤና ፅ/ቤት ሀላፌ ገልፀዋል፡፡