loading
የኒውዚ ላንዷ ጠቅላይ ሚንስትር ጀሲንዳ አርደርን በክሪስት ቸርች የጅምላ ግድያ ህዝባችውን ይቅርታ ጠየቁ::

አዲስ አበባ፣ ህዳር 29፣ 2013 የኒውዚ ላንዷ ጠቅላይ ሚንስትር ጀሲንዳ አርደርን በክሪስት ቸርች የጅምላ ግድያ ህዝባችውን ይቅርታ ጠየቁ:: ጠቅላይ ሚኒስትሯ ይቅርታ የጠየቁት ብሪንተን ታራንት የተባለው ትውልደ አውስትራሊያዊ ወጣት ያደረሰው የጅምላ ጭፍጨፋ ከጦር መሳሪያ ፈቃድ አሰጣጥ ጋር የተያያዘ ስህተት ነበር በማለት ነው፡፡ የሀገሪቱ የወንጀል መርማሪ ኮሚሽን ባወጣው መግለጫ ፖሊስ ግለሰቡ የጦር መሳሪያ ፈቃድ ሲሰጠው አስፈላጊውን ማጣራት […]

ሶማሊያ ለኬንያ ዜጎች ፈቅዳው የነበረውን የጉዞ መዳረሻ ቪዛ መከልከሏን ይፋ አደረገች::

አዲስ አበባ፣ ህዳር 29፣ 2013 ሶማሊያ ለኬንያ ዜጎች ፈቅዳው የነበረውን የጉዞ መዳረሻ ቪዛ መከልከሏን ይፋ አደረገች:: በሁለቱ ሀገራት መካከል በቅርቡ የጠፈጠረው የዲፕሎማሲ መሻከር ነወ ሶማሊያን ለዚህ ወሳኔ ያነሳሳት ተብሏል፡፡ የሶማሊያ ኢሚግሬሽንና ዜግነት ጉዳዮች ባለስልጣን መስሪያቤት ከዚህ በኋላ ወደ ሶማሊያ የሚጓዙ ኬንያዊያን አስቀድመው ቪዛ ማስመታት ይጠበቅባቸዋል ብሏል፡፡ አፍሪካ ኒውስ እንደዘገበው የዲፕሎማሲ ጉዙ የሚያደርጉ ግለሰቦች ሳይቀሩ ከሶማሊያ […]

የትግራይ ክልል ወደቀደመው መረጋጋትና ሰላም እየተመለሰ መሆኑ ተገለጸ::

አዲስ አበባ፣ ህዳር 30፣ 2013  የትግራይ ክልል ወደቀደመ ሰላሙና መረጋጋት እየተመለሰ መሆኑን የትግራይ ብልጽግና ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ነብዩ ስሁልሚካኤል አስታወቁ:: በክልሉ የመማር ማስተማር ሂደቱን ለማስጀመር የትምህርት ሚኒስቴር ተጨማሪ 50 ሚሊዮን ብር መመደቡን ገለጸዋል፡፡ አቶ ነብዩ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንዳስታወቁት፤ በህወሓት ቡድን ወደ አለመረጋጋት ገብቶ የነበረው የትግራይ ክልል አሁን ላይ ወደቀደመ ሰላምና መረጋጋቱ እየተመለሰ […]

አመንስቲ ኢንተርናሽናል አረጋዊያንን ከሽብርተኞች ጥቃት መጠበቅ ይገባል የሚል ጥሪ አቀረበ::

አዲስ አበባ፣ ህዳር 30፣ 2013  በተለያዩ ሀገራት የሚደርሱ የሽብር ጥቃቶች በእድሜ የገፉ አረጋዊያን ላይ እያደረሰ ያለው ጉዳት ለመከላከል ሁሉም የድርሻውን መወጣት አለበት ነው ያለው ተቋሙ፡፡ አፍሪካ ኒውስ እንደዘገበው በተለይ እንደ ናይጄሪያ፣ ማሊ፣ እንዲሁም በአብዛኛው የመካከለኛው አፍሪካ ሀገራት ችግሩ ከፋ ነው፡፡ የናይጄሪያው ፕሬዚዳንት ሙሃማዱ ቡሃሪ ገና ወደ ስልጣን በመጡ ማግስት ተደጋጋሚ የሽብር ጥቃት የሚያደርሰውን ቦኩ ሃራምን […]

ቤናሚን ኔታኒያሁ በፓርቲያቸው ውስጥ አዲስ የስልጣን ተቀናቃኝ ግለሰብ ተነስቶባቸዋል::

አዲስ አበባ፣ ህዳር 30፣ 2013 ቤናሚን ኔታኒያሁ በፓርቲያቸው ውስጥ አዲስ የስልጣን ተቀናቃኝ ግለሰብ ተነስቶባቸዋል:: በጠቅላይ ሚኒስትር ቤናሚን ኔታኒያ የሚመራው የሊኩድ ፓርቲ ሁነኛ ሰው የሆኑት ጌዲዮን ሳር ራሳቸውን ከፓርቲው ማግለላቸውን አስታውቀዋል፡፡ ለዚህ ምክንያታቸው ደግሞ ኔታኒያሁ ከሀገራቸው ይልቅ የራሳቸውን ጥቅም ያስቀድማሉ ስለዚህ ከሳቸው ጋር መስራት አልፈልግም የሚል ነው፡፡ ባለፈው ሳምንት የምርጫ ተቀናቃኛቸው የነበሩትና አብረዋቸው የጥምር መንግስት የመሰረቱት […]

በአምስት ወራት ውስጥ ከ1 ቢሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎች መያዙን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ::

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 06፣ 2013 በአምስት ወራት ውስጥ ከ1 ቢሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎች መያዙን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ:: የንግድ ውድድሩን ፍትሀዊ ለማድረግና የፀረ-ኮንትሮባንድ እንቅስቃሴውን ለመቆጣጠር የገቢዎች ሚኒስቴር እና የጉምሩክ ኮሚሽን ባደረጉት እንቅስቃሴ ነው እቃዎቹ የተያዙት፡፡ በዚህም ከሀምሌ እስከ ህዳር ባሉት አምስት ወራት ግምታዊ ዋጋቸው ከ1 ቢሊዮን 356 ሚሊዮን ብር በላይ የሆነ የወጪና የገቢ […]

ፕሬዚዳንት አላሳኒ ኦታራ ኮትዲቯርን ለሶስተኛ ጊዜ ለመምራት ቃለ መሃላ ፈፀሙ፡፡

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 06፣ 2013 ፕሬዚዳንት አላሳኒ ኦታራ ኮትዲቯርን ለሶስተኛ ጊዜ ለመምራት ቃለ መሃላ ፈፀሙ፡፡ በፈረንጆቹ ኦክቶበር 31 በተካሄደው ሀገራዊ ምርጫ ፕሬዚዳንት አላሳኒ ኦታራ 94 በመቶ በሆነ ድምፅ አሸንፈዋል መባሉን ተከትሎ ከረር ያለ ተቃውሞ ገጥሟቸው ነበር፡፡ ኦታራ ለሶስተኛ ጊዜ ለመወዳደር የህገ መንግስ ማሻሻያ ሲያደርጉ ጀምሮ ነበር በሀገሪቱ ተቃውሞው የተቀሰቀሰው፡፡ አልጀዚራ እንደዘገበው ኦታራ ተቃውሞውን አስተባብረዋል ያሏቸውን ተቃዋሚዎች […]

አሜሪካ ከሩሲያ የሚሳኤል መከላከያ ሲስተም ገዝታለች በሚል ምክንያት በቱርክ ላይ ማዕቀብ ጣለች::

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 06፣ 2013 አሜሪካ ከሩሲያ የሚሳኤል መከላከያ ሲስተም ገዝታለች በሚል ምክንያት በቱርክ ላይ ማዕቀብ ጣለች:: የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፒዮ ቱርክ ከሩሲያ የገዛችው የሚሳኤል መከላከያ ስርዓት ለአሜሪካ ደህንነት ስጋት መሆኑን ደጋግመን ነግረናት ነበር ብለዋል፡፡ ዋሽንግተን ያሳለፈችው ውሳኔ የቱርክን ወታራዊ አቅም የማዳከም ሳይሆን የራሷን ደህንነት የማስጠበቅ ነው በማለትም አክለዋል ፖምፒዮ፡፡ ቱርክ ባለፈው ጥቅምት ወር […]

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ለቴክኖሎጂ ቅርብ የሆነው ወጣት የዲጂታል እውቀት እንዲኖረው ለማድረግ እየሰራ መሆኑን አስታወቀ::

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 12፣ 2013 የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ለቴክኖሎጂ ቅርብ የሆነው ወጣት የዲጂታል እውቀት እንዲኖረው ለማድረግ እየሰራ መሆኑን አስታወቀ::ሚኒስቴሩ የጤና ጉዞ ወደ ኪቢቃሎ ተራራ በሚል በወልዲያ ከተማ ተራራ ላይ በተደረገው ጉዞ ላይ ለተሳተፉ ወጣቶች የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025ን አስተዋውቋል።የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር አህመዲን መሀመድ ለቴክኖሎጂ ቅርብ የሆነውን ወጣት የዲጂታል እውቀት እንዲኖረው ለማድረግ እየሰራን ነው ብለዋል። አብዛኞቹ […]

በህግ ማስከበር ዘመቻው ግዳጃቸውን በጀግንነት ለፈጸሙ የሰራዊቱ አባላት እውቅና እንደሚሰጥ ተገለጸ፡፡

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 13፣ 2013 በህግ ማስከበር ዘመቻው ግዳጃቸውን በጀግንነት ለፈጸሙ የሰራዊቱ አባላት እውቅና እንደሚሰጥ ተገለጸ፡፡ በትግራይ ክልል በተደረገው የህግ ማስከበር ዘመቻ ግዳጃቸውን በጀግንነት ለፈጸሙ የሰራዊቱ አባላት በየደረጃው እውቅና እንደሚሰጥ የጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹሙ ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ ገለጹ። የክልል ልዩ ሃይሎች በየቦታው የነበራቸው አስተዋጽ ከፍተኛ መሆኑንም አስታውቀዋል። ጠቅላይ ኤታማዦር ሹሙ ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ እንዳስታወቁት፤ በዚህ […]