loading
በኮትዲቯር ፕሬዚዳተታዊ ምርጫ ያሸነፉት አላሳኒ ኦታራ ለተቃዋሚዎች የውይይት ጥሪ አቀረቡ::

አዲስ አበባ፣ ህዳር 01፣ 2013 በኮትዲቯር ፕሬዚዳተታዊ ምርጫ ያሸነፉት አላሳኒ ኦታራ ለተቃዋሚዎች የውይይት ጥሪ አቀረቡ:: የሀገሪቱ ህገ መንግስታዊ ካውንስል በሰጠው ማረጋገጫ ኦታራ ለሶስተኛ ጊዜ አገሪቱን መምራት የሚያስችል ድምፅ አግኝተዋል፡፡ የ78 ዓመቱ ፕሬዚዳንት አላሳኒ ኦታራ በምርጫው 94 በመቶ የሚሆነውን የመራጮች ድምፅ አግኝተዋል ቢባልም ተቃዋሚዎች ውጤቱን አልተቀበሉትም፡፡ አልጀዚራ እንደዘገበው የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች ምርጫው ከጅምሩ ህገ መንግስታዊ ስላልሆነ […]

ጆ ባይደን ክትባት እስኪጀመር 200 ሺህ አሜሪካዊያን በኮሮናቫይረስ ሊሞቱ ይችላሉ ሲሉ አሰጠነቀቁ፡፡

አዲስ አበባ፣ ህዳር 01፣ 2013 ጆ ባይደን ክትባት እስኪጀመር 200 ሺህ አሜሪካዊያን በኮሮናቫይረስ ሊሞቱ ይችላሉ ሲሉ አሰጠነቀቁ፡፡ አዲሱ የአሜሪካ ተመራጭ ፕሬዚዳንት ይህን ያሉት አዲስ ከተቋቋመው የአሜሪካ የኮሮናቫይረስ አማካሪ ቦርድ ጋር ከተወያዩ በኋላ ነው፡፡ ባይደን 90 በመቶ ፈዋሽነቱ የተረጋገጠ ክትባት መኖሩን ከቦርዱ በተደረገላቸው ገለጻ መስማታቸውን እንደ መልካም ዜና ቢቆጥሩትም አሁንም ገና በርካታ ወራትን መጠበቅ ግድ ስለሚል […]

በአሜሪካ የጆ ባይደን መመረጥ በአፍሪካ ተስፋንም ጥርጣሬንም ይዞ መጥቷል ተባለ፡፡

አዲስ አበባ፣ ህዳር 02፣ 2013 በአሜሪካ የጆ ባይደን መመረጥ በአፍሪካ ተስፋንም ጥርጣሬንም ይዞ መጥቷል ተባለ፡፡ ጆ ባይደን አዲሱ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ሆነው መመረጣቸውን ተከትሎ ዋሽንግተን ከአፍሪካ ጋር ስለሚኖራት ግንኙነት ከወደዲሁ መላ መላ ምቶች ተበራክተዋል፡፡ አንዳንድ የአፍሪካ ሀገራት የባይደን ወደ ስልጣን መምጣት ለአህጉሪቱ ቀና አመለካት የላቸውም በሚባሉት ዶናልድ ትራምፕ ዘመን የሻከሩ ግንኙነቶች ይስተካከላሉ የሚል ተስፋ ሰንቀዋል፡፡ በተለይ […]

ክሬት በተባለችው የግሪክ ደሴት የተከሰተው የጎርፍ አደጋ በንብረት ላይ ትልቅ ውድመት አደረሰ::

አዲስ አበባ፣ ህዳር 02፣ 2013 ክሬት በተባለችው የግሪክ ደሴት የተከሰተው የጎርፍ አደጋ በንብረት ላይ ትልቅ ውድመት አደረሰ:: የደሴቷ ባለ ስልጣናት እንዳሉት የመንገድ አውታሮች ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ በአደጋው ወድመዋል፡፡ ዩሮ ኒውስ እንደዘገበው ጎርፉ በርካታ ቤቶችን ከማጥለቅለቁ በሻገር ተሸከርካሪዎችን ወደ በባህር ሲወስዳቸው ታይቷል፡፡ ጎርፉ በርካታ የመሰረተ ልማቶች ላይ ከባድ ጉዳት ቢያደርስም እስካሁን በሰው ህይዎት ላይ የደረሰ […]

አንግሊዝ በኮቪድ-19 ብዙ ዜጎች ከሞቱባቸው የአውሮፓ ሀገራት ቀዳሚ ሆነች::

አዲስ አበባ፣ ህዳር 03፣ 2013 አንግሊዝ በኮቪድ-19 ብዙ ዜጎች ከሞቱባቸው የአውሮፓ ሀገራት ቀዳሚ ሆነች:: በመላው ዓለም ዳግም ያገረሸው የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ከአውሮፓ ሀገራት በተለይ እንግሊዝን ክፉኛ እያጠቃት መሆኑ ተሰምቷል፡፡ ዩሮ ኒውስ እንደዘገበው በንግሊዝ በ24 ሰዓታት ውስጥ ወደ ስድስት መቶ የሚጠጉ ሰዎ በቫይረሱ ሳቢያ ህይዎታቸው አልፏል፡፡ ይህም በሀገሪቱ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ50 ሺህ በላይ […]

በየመን ለደረሰው ቀውስ ዓለም ዝምታን መምረጡ እንዳሳሰበው የመንግስታቱ ድርጅት ገለፀ::

አዲስ አበባ፣ ህዳር 03፣ 2013 በየመን ለደረሰው ቀውስ ዓለም ዝምታን መምረጡ እንዳሳሰበው የመንግስታቱ ድርጅት ገለፀ:: ድርጅቱ ባወጣው ሪፖርት በየመን በእርስበርስ ውጊያ ሳቢያ የተከሰተው ርሃብ እድሚያቸው ከአምስት ዓመት በታች የሆኑ 100 ሺህ ህፃናትን ህይዎት አደጋ ላይ ጥሏል፡፡ ሚድል ኢስት ሞኒተር የተባበሩት መንግስታት ድርጅትን ጠቅሶ እንደዘገበው ሁኔታው በዚሁ የሚቀጥል ከሆነ የመን በዚህ ችግር ምክንያት አንድ ትውልድ ልታጣ […]

የአልጀሪያው ፕሬዚዳንት የኮቪድ-19 ህክምናቸውን አጠናቀቁ::

አዲስ አበባ፣ ህዳር 07፣ 2013 የአልጀሪያው ፕሬዚዳንት የኮቪድ-19 ህክምናቸውን አጠናቀቁ::ባለፈው ኦክቶበር ወር መጨረሻ ላይ ተመርምረው ቫይረሱ እንዳለበባቸው ያወቁት ፕሬዚዳንት አብደልመጂድ ቲቦኒ ለህክምና ክትትል ወደ ጀርመን ተጉዘው ነበር ተብሏል፡፡ ቲቦኒ ከዚህ በኋላ ተበቤተ መንግስታቸው ሆነው ጨማሪ የህክምና ክትትሎች እንደሚደረጉላቸው ከፕሬዚዳንቱ ቢሮ አስታውቋል፡፡ ሚድል ኢስት ሞኒተር እንደዘገበው ፕሬዚዳንቱ ያሉበትን ሁኔታ አስመልክተው ለዘህዝቡ መግለጫ እንዲሰጡ ቢሯቸው ወስኗል፡፡ ቲቦኒ […]

አሜሪካ በአንድ ሳምንት አንድ ሚሊዮን ሰዎች በኮሮናቫይረስ መያዛቸውን ተሰማ::

አዲስ አበባ፣ ህዳር 07፣ 2013 አሜሪካ በአንድ ሳምንት አንድ ሚሊዮን ሰዎች በኮሮናቫይረስ መያዛቸውን ተሰማ:: የኮሮናቫይረስ ስርጭት እንደአዲስ የተባባሰባት አሜሪካ በየቀኑ ከ100 ሺህ በላይ ሰዎች በበሽታው እንደሚያዙ እየተነገረ ይገኛል፡፡ በዚህም የተነሳ አሁን ላይ በሀገሪቱ በኮቪድ-19 ወረርሽ የተያዙ ሰዎች ከ11 ሚሊዮን በላይ መድረሱ ነው የተነገረው፡፡ ቢቢሲ እንደዘገበው አሜሪካ በተለያዩ ግዛቶች አገልግሎት ሰጭ ተቋማትን የመዝጋት እርምጃዎችን ለመወሰድ ተገዳለች፡፡ […]

በኮቪድ 19 ምክንያት የትጎዱ የቱሪዝም አገልግሎት ሰጪዎችን ለመደገፍ እና ለማነቃቃት ያለመ የ30 ኪ.ሜ የብስክሌት ውድድር ማዘጋጀቱን ቱሪዝም ኢትዮጵያ አስታወቀ።

አዲስ አበባ፣ ህዳር 07፣ 2013 በኮቪድ 19 ምክንያት የትጎዱ የቱሪዝም አገልግሎት ሰጪዎችን ለመደገፍ እና ለማነቃቃት ያለመ የ30 ኪ.ሜ የብስክሌት ውድድር ማዘጋጀቱን ቱሪዝም ኢትዮጵያ አስታወቀ።ከዚህ ቀደም በቱሪዝም ዘርፍ ተሰማርተው የነበሩ ባለሀብቶች እና አገልግሎት ሰጪዎች በኮቪድ ምክንያት ተስፋ ቆርጠው ከዘርፉ በመውጣት ላይ ይገኛሉ በዚህም ምክንያት የቱሪዝም ዘርፉን ለማነቃቃት እና ወደ ስራ ለማስገባት ያለመ የተራራ ላይ ቱሪዝም ማዘጋጀቱን […]

መንግስት ወደ ጎረቤት ሀገራት የሚሰደዱ ዜጎችን ለመቀበል ዝግጁ መሆኑን ጠ/ሚ ዐቢይ አስታወቁ::

አዲስ አበባ፣ ህዳር 08፣ 2013 መንግስት ወደ ጎረቤት ሀገራት የሚሰደዱ ዜጎችን ለመቀበል ዝግጁ መሆኑን ጠ/ሚ ዐቢይ አስታወቁ:: የኢትዮጵያ መንግስት ወደ ጎረቤት ሀገራት የሚሰደዱ ወገኖችን ለመቀበል እና ወደ ቀዬአቸው ለመመለስ ዝግጁ መሆኑን ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ የገለፁት፡፡ ጠቅላይ ሚኒስት ዐቢይ በትዊተር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት የተሰደዱ ንፁሀን ዜጎችን ንብረታቸውን ለመጠበቅ ፣ በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የሰብአዊ ድጋፍ ለማቅረብ እና […]