loading
የኮሮና ቫይረስ በሀገራችን ከተከሰተ ግዜ ጀመሮ በራስ ተነሳሽነት የሚደረግ ትምህርት ወይም ሰልፍ ለርኒግ መጨመሩን የደብረ ታቦር ዩንቨርስቲ ፕሬዚዳንት ገለፁ::

አዲስ አበባ፣ሐምሌ28፣ 2012  የኮሮና ቫይረስ በሀገራችን ከተከሰተ ግዜ ጀመሮ በራስ ተነሳሽነት የሚደረግ ትምህርት ወይም ሰልፍ ለርኒግ መጨመሩን የደብረ ታቦር ዩንቨርስቲ ፕሬዚዳንት ገለፁ::ሰልፍ ለርኒግ ወይም እራስን በራስ የማሰተማር ስራ የኮቪድ 19 በሀገራችን ከተከሰተ ግዜ ጀምሮ በተለያዩ ዩንቨርስቲዎች መታየቱን ፕሬዝዳንቱ ገልፀዋል፡፡ዓለማት እራስን በራስ ከማስተማር ጋር ተያይዞ ረዥም ርቀት መጓዛቸውን የገለፁት ፕሬዝዳንቱ እንደ እትዮጵያ ባሉ በማደግ ላይ በሚገኙ […]

በደቡብ ኮሪያ ደራሽ ጎርፍ እና የመሬት መንሸራተት 13 ሰዎችን ገደለ::

አዲስ አበባ፣ሐምሌ28፣ 2012 በደቡብ ኮሪያ ደራሽ ጎርፍ እና የመሬት መንሸራተት 13 ሰዎችን ገደለ:: በዋና ከተማዋ ሴኡል አቅራቢያ በሚገኙ አካባዎች የተከሰተው የተፈጥሮ አደጋ ከሟቾቹ በተጨማሪ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ቤት ንብረታቸውን ትተው እንዲፈናቀሉ አድርጓል ነው የተባለው፡፡ አንድ የ60 ዓመት አዛውንትን ጨምሮ 13 ሚሆኑ ሰዎች የገቡበት እንዳልታወቀም አልጀዚራ በዘገባው አስነብቧል፡፡ ጎርፉ ከ5 ሺህ ሄክታር በላይ የእርሻ መሬት እና […]

የዓለም ጤና ድርጅት በቀጣዮቹ አምስት ወራት በኮቪድ 19 የሚያዙ ወጣቶች ቁጥር በሦስት እጥፍ ያድጋል ሲል አሳሰበ፡፡

አዲስ አበባ፣ሐምሌ29፣ 2012 የዓለም ጤና ድርጅት በቀጣዮቹ አምስት ወራት በኮቪድ 19 የሚያዙ ወጣቶች ቁጥር በሦስት እጥፍ ያድጋል ሲል አሳሰበ፡፡በዓለም አቀፍ የሚገኙ እድሜያቸው ከ15 እስከ 24 ዓመት የሆናቸው ወጣቶች በቫይረሱ የመያዝ እድላቸው በቀጣዮቹ አምስት ወራት ውስጥ በሶስት እጥፍ ያድጋል ብሏል ድርጅቱ፡፡ በቫይረሱ ስርጭት የመጀመሪያውን ስፍራ የያዘቸው አሜሪካን ጨምሮ ስፔን፣ጀርመን፣ ፈረንሳይና ጃፓን አዲስ በቫይረሱ ከሚያዙት ሰዎች መካከል […]

ግብፅ በግድቡ ዙሪያ በቅርቡ የተጀመረውን ድርድር ለጊዜው ጥላ የመውጣት ሀሳብ እንዳላት ተገለፀ::

አዲስ አበባ፣ሐምሌ29፣ 2012 ግብፅ በግድቡ ዙሪያ በቅርቡ የተጀመረውን ድርድር ለጊዜው ጥላ የመውጣት ሀሳብ እንዳላት ተገለፀ:: ካይሮ ይህን ለማድረግ ያሰበችው በግድቡ አሞላል ሂደት በኢትዮጵያ በኩል የቀረበውን የድርድር ሀሳብ መጀመሪያ የውስጥ ምክክር ላድርግበት በሚል ነው ተብሏል፡፡ የግብፅ የውሃ ሚኒስቴር በሰጠው መግለጫ ኢትዮጵያ ያቀረበችው አዲስ የመደራደሪያ ረቂቅ ሀሳብ ሀግና መመሪያን ያከበረ አይደለም ብሏል፡፡ ሚኒስቴሩ አክሎም በአዲስ አበባ በኩል […]

በዲሞክራቲክ ኮንጎ ባለፉት ሰድስት ወራት ብቻ ከ1 ሺህ 300 ሰዎች በታጣቂዎች ተገድለዋል ተባለ::

አዲስ አበባ፣ሐምሌ30፣ 2012  በዲሞክራቲክ ኮንጎ ባለፉት ሰድስት ወራት ብቻ ከ1 ሺህ 300 ሰዎች በታጣቂዎች ተገድለዋል ተባለ:: የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ቢሮ ባወጣው ሪፖርት እንዳለው 165 ህፃናትን ጨምሮ 1 ሺህ 315 ሰዎች ነፍጥ አንግበው በሚንቀሳቀሱ ሸማቂዎች ተገድለዋል፡፡በሀገሪቱ በተለይ በምስራቃዊ ኮንጎ ከጊዜ ወደ ጊዜ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት እየተባባሰ መምጣቱን ድርጅቱ ገልጿል፡፡ አልጀዚራ እንደዘገበው በዲሞክራቲክ ሪብሊክ ኮንጎ […]

በሊባኖስ የሟቾች ቁጥር ከ130 በላይ ሲደርስ የቆሰሉ ሰዎች ከ5 ሺህ በላይ መሆናቸው ተነግሯል::

አዲስ አበባ፣ሐምሌ30፣ 2012በሊባኖስ የሟቾች ቁጥር ከ130 በላይ ሲደርስ የቆሰሉ ሰዎች ከ5 ሺህ በላይ መሆናቸው ተነግሯል:: በወደብ ተከማችቶ በነበረ ኬሚካል ፍንዳታ ሳቢያ ከሞቱት እና ከቆሰሉት ሰዎች ባሻገር 300 ሺህ ሊባኖሳዊያን ቤት አልባ መሆናቸውን የሀገሪቱ ቴሌቭዥን ዘግቧል፡፡ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች አሁንም በህንፃዎች ፍርስረሾች ስር ተቀብረው የቀሩ ሰዎችን ለማግኘት ፍለጋቸውን አጠናክረው እንደቀጠሉ ናቸው፡፡ ሮይተርስ እንደዘገበው በተከሰተው ፍንዳታ ምክንያት […]

በሐረሪ ክልል ከ12 ሺህ በላይ ሰዎች ተደራሽ የሚያደርግ የኮሮረና ቫይረስ ምርመራ ዘመቻ ነሃሴ 1 እንደሚጀመር የክልሉ ጤና ጥበቃ ቢሮ አስታወቀ ።

አዲስ አበባ፣ሐምሌ30፣ 2012 በሐረሪ ክልል ከ12 ሺህ በላይ ሰዎች ተደራሽ የሚያደርግ የኮሮረና ቫይረስ ምርመራ ዘመቻ ነሃሴ 1 እንደሚጀመር የክልሉ ጤና ጥበቃ ቢሮ አስታወቀ ። የክልሉ ጤና ጥበቃ ቢሮ ምክትል ሀላፊና የኮሮና መከላከል ግብረሃይል ጸሃፊ አቶ ፈቲህ መሀዲ በሰጡት መግለጫ በክልሉ በአሁኑ ወቅት ስርጭቱ እየጨመረ ያለው የኮሮና ቫይረስ ለመቆጣጠር ዘርፈ ብዙ ተግባራት እየተከናወኑ ይገኛሉ። በተለይም ከነገ […]

በአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ኦዲት እና ምዝገባ ሊጀመር መሆኑ ተገለፀ።

አዲስ አበባ፣ሐምሌ30፣ 2012 በአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ኦዲት እና ምዝገባ ሊጀመር መሆኑ ተገለፀ።ምዝገባው ህገ ወጥ የመሬት ወረራን ለመከላከል ያለመ መሆኑንም የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ጽህፈት ቤት መረጃ ያመለክታል።የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ክንቲባ ኢንጂር ታከለ ኡማ የምዝገባ እና ኦዲት ሂደቱን በተመለከተ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አድርገዋል። ከነገ ጀምሮ መካሄድ የሚጀምረው የምዝገባ እና ኦዲት ሥራ ከመሃል ከተማ […]

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በቤይሩት የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ድጋፍ እንዲያገኙ እየሰራሁ ነው አለ::

አዲስ አበባ፣ነሐሴ1፣ 2012 የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በቤይሩት የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ድጋፍ እንዲያገኙ እየሰራሁ ነው አለ:: በሊባኖስ በደረሰዉ ፍንዳታ የ1 ኢትዮጵያዊ ህይወት ማለፉንና 9 ኢትዮጵያዊያን ደግሞ ቀላልና ከባድ አደጋ እንደደረሰባቸዉ የሚኒስሩ ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲን ሙፍቲ ገልፀዋል፡፡ በቤይሩት በሚገኙት መጠለያዎች ዉስጥ ያሉ ኢትዮጵያዊያን ግን ጉዳት እንዳልደረሰባቸዉና በጥሩ ደህንነት እንደሚገኙ ነዉ የተነገረ ሲሆን ወደ ፌት ግን ቁጥሩ ሊጨምር […]

በሱዳን የተከሰተ የጎርፍ አደጋ 10 ሰዎችን ሲገድለ ከ3 ሺህ በላይ በሚሆኑ ቤቶች ላይ ጉት አድርሷል ተባለ::

አዲስ አበባ፣ነሐሴ1፣ 2012 በሱዳን የተከሰተ የጎርፍ አደጋ 10 ሰዎችን ሲገድለ ከ3 ሺህ በላይ በሚሆኑ ቤቶች ላይ ጉት አድርሷል ተባለ:: አደጋው የደረሰው በደቡባዊ ምስራቅ የሀገሪቱ ክፍል በምትገኘው ብሉ ናይል ግዛት ሲሆን በስፍራው የሚገኝ ግድብ በመደርመሱ ውሃው አካባቢውን በማጥለቅለቁ ነው ተብሏል፡፡ አፍሪካ ንውስ እንደዘገበው በውሃ ሙላቱ ጉዳት ከደረሰባቸው ከ300 በላይ ቤቶች መካከል 1 ሺህ 800 የሚሆኑት ሙሉ […]