loading
በጥቂት ዓመታት በመላው ኢትዮጵያ 20 ቢሊዮን ችግኞች  እንደሚተከሉ  ጠቅላይ ሚኒሰትር ዐቢይ ተናገሩ፡፡

በጥቂት ዓመታት በመላው ኢትዮጵያ 20 ቢሊዮን ችግኞች  እንደሚተከሉ  ጠቅላይ ሚኒሰትር ዐቢይ ተናገሩ፡፡ አዲስ አበባ፣ ግንቦት 5፣ 2012 ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት፣ የዚህን ዓመት የ አረንጓዴ አሻራ   የችግኝ ተከላ ቅድመ ዝግጅት በተመለከተ የግብርና ሚኒስቴር ማብራሪያ አቅርቧል፡፡የብሔራዊ አስተባባሪ ኮሚቴው አባላት፣ የቴክኒክ ኮሚቴ አባላት፣ የክልል ፕሬዚደንቶች፣ ሕዝቡን የማነሳሳት ሥራን የሚከውኑ ተጽዕኖ አሳዳሪ ግለሰቦችን ጨምሮ ዐበይት ባለድርሻ አካላት ተሳትፈውበታል፡፡ባለፈው […]

በአዲስ አበባ የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል ያላደረጉ ሰዎችን ማሰር መጀመሩን ፖሊስ አስታወቀ ።

በአዲስ አበባ የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል ያላደረጉ ሰዎችን ማሰር መጀመሩን ፖሊስ አስታወቀ ። አዲስ አበባ፣ ግንቦት 5፣ 2012  የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን  እንዳለው በአስቸኳይ አዋጁ መሰረት ለኮሮና ቫይረስ መከላከያ የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል ሁሉም ሰው የግድ መጠቀም ባለበት ሰዓት እንዲጠቀም ያስገድዳል።በዚህም መሰረት የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብልጭንብል ያላደረጉ ሰዎች በፖሊስ በመታሰር ላይ ናቸው።የኮሚሽኑ […]

በኢትዮጵያ ወጣቶች ለኮሮና ቫይረስ ይበልጥ ተጋላጭ መሆናቸዉን የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዮትአስታወቀ፡፡

በኢትዮጵያ ወጣቶች ለኮሮና ቫይረስ ይበልጥ ተጋላጭ መሆናቸዉን የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዮትአስታወቀ፡፡ አዲስ አበባ፣ ግንቦት 5፣ 2012  ኢንስቲትዩቱ እንዳስታወቀዉ በኢትዮጵያ አስከ ማክሰኞ ዕለት በኮሮና ቫይረስ ከተያዙ 261   ሰዎች መካከል 91 የሚሆኑት እድሜያቸዉ ከ15- 24 ዓመት መሆኑን የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዮት ያወጣዉ አህዛዊ መረጃ ይጠቁማል፡፡ከ25 -34 ባሉት የእድሜ ክልል ዉስጥ ያሉት ደግሞ በሁለተኛ ደረጃ ተጋላጭ  መሆናቸዉን ነዉ መረጃዉ ያመላከተዉ […]

ጀርመን የኮሮና ወረርሽኝን ለመከላከል የቁሳቁስ ድጋፍ አደረገች::

ጀርመን የኮሮና ወረርሽኝን ለመከላከል የቁሳቁስ ድጋፍ አደረገች:: አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 5 ፣ 2012 የጀርመን መንግሥት በኢትዮጵያ የኮሮና ወረርሽኝን ለመከላከል የቁሳቁስ ድጋፉን ለሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አስረክቧል።ድጋፉ በኢትዮጵያ የኮሮና ወረርሽን ለመከላከል ተግባራዊ ካደረጋቸው የድጋፍ ማዕቀፎች መካከል አንዱ  መሆኑ ተገልጿል።በኢትዮጵያ የጀርመን አምባሳደር ብሪታ ዋግነር ለሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትሯ ፕሮፌሰር ሒሩት ወልደማሪያም ነዉ ድጋፉን ያስረከቡት ፡፡ቫይረሱ በዓለም ላይ ጉዳት እያደረሰ መሆኑን  ያስታወሱት አምባሳደሯ፤አገራቸው ኢትዮጵያን ለመርዳት ድጋፉን ማድረጓን ገልጸዋል። የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትሯ ፕሮፌሰር ሒሩት ወልደማሪያም በዚሁ ወቅት እንደገለጹት ጀርመን የኮሮና ወረርሽኝን ለመዋጋት ላደረገችው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።ፕሮፌሰርሂሩት፤ሳሙና የእጅ መታጠቢያ 213 ሺህ ኢንፍራሬድ ቴርሞሜትር 50 ያሕል ሰራተኞችችን ከቤታቸው ሆነው እንዲሰሩ የሚያስች ዋይፋ አፓራተስ አበርክተውልናል። እነዚህ ቁሳቁስ ለቴክኒክና ሙያ ተቋሞችና ለዩኒቨርሲቲዎች የምናሰራጫቸው ይሆናል።ብለዋልድጋፉ በትምህርት ተቋማት ወረርሽኙን ለመከላከል የሚደረገውን ጥረት እንደሚያግዝ ተገልጿል፡፡

ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውርን በመቆጣጠር በኩል ውጤታማ ስራ ተከናውኗል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ገለፁ::

አዲስ አበባ፣ግንቦት6፣2012 ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውርን በመቆጣጠር በኩል ውጤታማ ስራ ተከናውኗል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ገለፁ:: ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ባለፉት ጥቂት ወራት ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውርን በመቆጣጠር በኩል ውጤታማ ስራ መከናወኑን ገለጹ።ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፌስቡክ ገፃቸው ባስተላለፉት መልእክት ባለፉት ጥቂት ወራት ሕገ ወጥ የጦር መሣሪያ አዘዋዋሪዎችን ተከታትሎ በመያዝ አኩሪ ሥራ ተሠርቷል። […]

በኢትዮጵያ በ24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ የላቦራቶሪ መምርመራ 14 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 11፣ 2012 በኢትዮጵያ በ24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ የላቦራቶሪ መምርመራ 14 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር በመግለጫው እንዳስታወቀው በ24 ሰዓታት ውስጥ በ3 ሺህ 271 ሰዎች ላይ በተደረገ ምርመራ ነው ታማሚዎቹ የተለዩት፡፡ በቫይረሱ የተያዙት ሁሉም ኢትዮጵያዊያን ሲሆኑ እድሜያቸው ከ9 እስከ 65 ዓመት የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ 11 ወንዶችና 3 ሴቶች መሆናቸው ታውቋል፡፡ በምርመራ […]

ኮቪድ 19ን ተከላክለን የተሻለች ሀገር ለመገንባት ባለን ሀብት ላይ እውቀትና ፈጠራን አቀናጅተን መጠቀም ይኖርብናል አሉ ጠ/ሚ ዐቢይ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 11፣ 2012 ኮቪድ 19ን ተከላክለን የተሻለች ሀገር ለመገንባት ባለን ሀብት ላይ እውቀትና ፈጠራን አቀናጅተን መጠቀም ይኖርብናል አሉ ጠ/ሚ ዐቢይ:: ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በፌስቡክ ገፃቸው ፈጠራን በተመለከተ ባስተላለፉት መልእክት፥ ብዙዎቹ የፈጠራ ውጤቶች የፈተና ልጆች ናቸው ይባላል ብለዋል። የሰው ልጆች ከዛሬው ሥልጣኔያቸው ላይ የደረሱት በየዘመናቱ የተደቀኑባቸውን እንቅፋቶች ለማለፍ እውቀትና ክሎታቸውን በስፋት በመጠቀማቸው […]

ለኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ ቀጥሏል::

ለኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ ቀጥሏል ። የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ወደ ወሳኝ ምዕራፍ በተሸጋገረበት ወቅት የህዝቡ ሁለንተናዊ ተሳትፎ እያደገ መምጣቱን የአማራ ክልል የታላቁ ህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት አስታወቀ። የጽህፈት ቤቱ ሃላፊ አቶ ላቀ ጥላዬ ለኢዜአ እንደገለጹት የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ማጠናቀቅ የአገራችን ሉአላዊነትና የፍትሃዊ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ ጉዳይ ነው። መንግስትና ህዝብ […]

የደቡብ ሱዳኑ ተቀዳሚ ምክትል ፐሬዚዳንት ሪክ ማቻር በተደረገላቸው ምርመራ የኮሮናቫይረስ ተገኘባቸው::

የደቡብ ሱዳኑ ተቀዳሚ ምክትል ፐሬዚዳንት ሪክ ማቻር በተደገላቸው ምርመራ የኮሮናቫይረስ ተገኘባቸው:: ሲጂ ቲ ኤን በዘገባው እንዳስነበበው የሀገሪቱ የመከላከያ ሚኒስትር ሆነው በማገልገል ላይ ያሉት የማቻር ባለቤት አንጀሊና ቴኒም በቫይረሱ መጠቃታቸው ታውቋል፡፡የማቻር ፕሬስ ሴክሬተሪ ጀምስ ጋትዴት ዳክ እንዳሉት የቢሮ ሰራተኞቻቸው እና የግል ጠባቂዎቻቸው ጭምር በኮቪድ 19 መያዛቸው ተረጋግጧል፡፡ ምትል ፕሬዚዳንቱ በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን በይፋ ለህዝብ መናገራቸውን እና […]

የብሩንዲ የምርጫ ኮሚሽን ተቀናቃኝ ፖለቲከኞች የድምፅ ቆጠራ ውጤቱን በትግዕስት እንዲጠብቁ ጥሪ አቀረበ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 14፣2012 የብሩንዲ የምርጫ ኮሚሽን ተቀናቃኝ ፖለቲከኞች የድምፅ ቆጠራ ውጤቱን በትግዕስት እንዲጠብቁጥሪ አቀረበ ብሩንዲያዊያን ባለፈው ረቡዕ የኮሮና ቫይረስ ወረረሽኝ ሳያስፈራቸው የወደፊት ፕሬዚዳንታቸውን ወደ ስልጣን ለማምጣት የሚያስችላቸውን ድምፅ ሲሰጡ ታይተዋል፡፡ የብሩንዲ ብሄራዊ ገለልተኛ የምርጫ ኮሚሽን ቆጠራው ገና ቀናትን ስለምወስድ ከወዲሁ የሚተላለፉ የአሸናፊነት መልእክቶች እንዲቆሙ ማሳሰቢያ ሰጥቷል፡፡ ይሁን እና የተቃዋሚ መሪው አጋቶን ሩዋሳ የድምጽ ቆጠራው […]