loading
በጥቂት ዓመታት በመላው ኢትዮጵያ 20 ቢሊዮን ችግኞች  እንደሚተከሉ  ጠቅላይ ሚኒሰትር ዐቢይ ተናገሩ፡፡

በጥቂት ዓመታት በመላው ኢትዮጵያ 20 ቢሊዮን ችግኞች  እንደሚተከሉ  ጠቅላይ ሚኒሰትር ዐቢይ ተናገሩ፡፡ አዲስ አበባ፣ ግንቦት 5፣ 2012 ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት፣ የዚህን ዓመት የ አረንጓዴ አሻራ   የችግኝ ተከላ ቅድመ ዝግጅት በተመለከተ የግብርና ሚኒስቴር ማብራሪያ አቅርቧል፡፡የብሔራዊ አስተባባሪ ኮሚቴው አባላት፣ የቴክኒክ ኮሚቴ አባላት፣ የክልል ፕሬዚደንቶች፣ ሕዝቡን የማነሳሳት ሥራን የሚከውኑ ተጽዕኖ አሳዳሪ ግለሰቦችን ጨምሮ ዐበይት ባለድርሻ አካላት ተሳትፈውበታል፡፡ባለፈው […]

በአዲስ አበባ የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል ያላደረጉ ሰዎችን ማሰር መጀመሩን ፖሊስ አስታወቀ ።

በአዲስ አበባ የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል ያላደረጉ ሰዎችን ማሰር መጀመሩን ፖሊስ አስታወቀ ። አዲስ አበባ፣ ግንቦት 5፣ 2012  የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን  እንዳለው በአስቸኳይ አዋጁ መሰረት ለኮሮና ቫይረስ መከላከያ የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል ሁሉም ሰው የግድ መጠቀም ባለበት ሰዓት እንዲጠቀም ያስገድዳል።በዚህም መሰረት የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብልጭንብል ያላደረጉ ሰዎች በፖሊስ በመታሰር ላይ ናቸው።የኮሚሽኑ […]

በኢትዮጵያ ወጣቶች ለኮሮና ቫይረስ ይበልጥ ተጋላጭ መሆናቸዉን የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዮትአስታወቀ፡፡

በኢትዮጵያ ወጣቶች ለኮሮና ቫይረስ ይበልጥ ተጋላጭ መሆናቸዉን የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዮትአስታወቀ፡፡ አዲስ አበባ፣ ግንቦት 5፣ 2012  ኢንስቲትዩቱ እንዳስታወቀዉ በኢትዮጵያ አስከ ማክሰኞ ዕለት በኮሮና ቫይረስ ከተያዙ 261   ሰዎች መካከል 91 የሚሆኑት እድሜያቸዉ ከ15- 24 ዓመት መሆኑን የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዮት ያወጣዉ አህዛዊ መረጃ ይጠቁማል፡፡ከ25 -34 ባሉት የእድሜ ክልል ዉስጥ ያሉት ደግሞ በሁለተኛ ደረጃ ተጋላጭ  መሆናቸዉን ነዉ መረጃዉ ያመላከተዉ […]

ጀርመን የኮሮና ወረርሽኝን ለመከላከል የቁሳቁስ ድጋፍ አደረገች::

ጀርመን የኮሮና ወረርሽኝን ለመከላከል የቁሳቁስ ድጋፍ አደረገች:: አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 5 ፣ 2012 የጀርመን መንግሥት በኢትዮጵያ የኮሮና ወረርሽኝን ለመከላከል የቁሳቁስ ድጋፉን ለሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አስረክቧል።ድጋፉ በኢትዮጵያ የኮሮና ወረርሽን ለመከላከል ተግባራዊ ካደረጋቸው የድጋፍ ማዕቀፎች መካከል አንዱ  መሆኑ ተገልጿል።በኢትዮጵያ የጀርመን አምባሳደር ብሪታ ዋግነር ለሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትሯ ፕሮፌሰር ሒሩት ወልደማሪያም ነዉ ድጋፉን ያስረከቡት ፡፡ቫይረሱ በዓለም ላይ ጉዳት እያደረሰ መሆኑን  ያስታወሱት አምባሳደሯ፤አገራቸው ኢትዮጵያን ለመርዳት ድጋፉን ማድረጓን ገልጸዋል። የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትሯ ፕሮፌሰር ሒሩት ወልደማሪያም በዚሁ ወቅት እንደገለጹት ጀርመን የኮሮና ወረርሽኝን ለመዋጋት ላደረገችው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።ፕሮፌሰርሂሩት፤ሳሙና የእጅ መታጠቢያ 213 ሺህ ኢንፍራሬድ ቴርሞሜትር 50 ያሕል ሰራተኞችችን ከቤታቸው ሆነው እንዲሰሩ የሚያስች ዋይፋ አፓራተስ አበርክተውልናል። እነዚህ ቁሳቁስ ለቴክኒክና ሙያ ተቋሞችና ለዩኒቨርሲቲዎች የምናሰራጫቸው ይሆናል።ብለዋልድጋፉ በትምህርት ተቋማት ወረርሽኙን ለመከላከል የሚደረገውን ጥረት እንደሚያግዝ ተገልጿል፡፡