loading
በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከመቐለ የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል

የሊጉ የ22ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ዛሬ በክልል እና አዲስ አበባ ስታዲየሞች ይከናወናሉ፡፡ ከአንድ ጨዋታ በስተቀር ሌሎች ግጥሚያዎች ክልል ላይ ይደረጋሉ፡፡ ክልል ላይ የሚከወኑት እነዚህ ጨዋታዎች በተመሳሳይ 9፡00 ይደረጋሉ፡፡ አዳማ ከተማ በአዳማ አበበ ቢቂላ ስታዲየም ላይ በአሰልጣኝ ገዛህኝ ከተማ የሚሰለጥነውን ኢትዮጵያ ቡና የሚገጥም ይሆናል፡፡ ባህር ዳር ከነማ በግዙፉ የከተማው ስታዲየም ከሊጉ ላለመውረድ እየተፍጨረጨረ የሚገኘውን ደቡብ ፖሊስ ያስተናግዳል፡፡ […]

መንግሥት የሚደጉመው የፓልም ዘይት የጤናችግር  ስለሚያመጣ በሌሎች ፈሳሽ ዘይቶች እንዲቀየር ጤና ሚኒስቴር ጠየቀ

መንግሥት የሚደጉመው የፓልም ዘይት የጤናችግር  ስለሚያመጣ በሌሎች ፈሳሽ ዘይቶች እንዲቀየር ጤና ሚኒስቴር ጠየቀ። ከፍተኛ የጤና ችግር ያመጣል የተባለው የፓልም ዘይት ከ90 እስከ 95 በመቶ በድጎማ የሚገባ ሲሆን፣ ይህንን ለመቀየር መጠየቁን ነው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ያስታወቀው፡፡ ሚኒስቴሩ የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩትና የመድኃኒትና ምግብ ቁጥጥር ባለሥልጣን ያቀረባቸውን ጥናቶች ምክረ ሐሳብ መሠረት በማድረግ፣ የፓልም ዘይት በፈሳሽ ዘይቶች እንዲቀየር ለጠቅላይ […]

አንድ የቦይንግ ምርት የሆነ አውሮፕላን በረራ ከጀመረ በኋላ በአውሮፕላኑ ጅራት ላይ እሳት መፍጠሩ ተሰማ

አንድ የቦይንግ ምርት የሆነ አውሮፕላን በረራ ከጀመረ በኋላ በአውሮፕላኑ ጅራት ላይ እሳት መፍጠሩ ተሰማ። ባለቤትነቱ የኤር ዚምባብዌ  የሆነ ቦይንግ-ሰራሽ የቦይንግ 767-200ኤር አውሮፕላን ነው ሞተሩ በሚገኝበት የአውሮፕላኑ ጅራት ላይ  እሳት የፈጠረው፡፡ ይህ አውሮፕላን ከደቡብ አፍሪካ ጆሃንስበርግ አየር ማረፊያ  ከተነሳ በኋላ  ነው ብልሽቱ እና የእሳት ብልጭታው የታየው ሲል የሃገሪቱ አየር መንገድ ያስታወቀው፡፡ በብልሽቱ በረራው አለመስተጓጉሉና አውሮፕላኑ ሀራሬ በሰላም ደርሶ ማረፉን ኤር ዚምባብዌ ገልጿል፡፡ የዙምባቡዌ አየር መንገድ የብልሽቱን መንስኤ ለማወቅ ምርመራ እያካሄደ መሆኑን ገልጿል፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ከጤና ባለሙያዎች ጋር ሊወያዩ ነው

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ከጤና ባለሙያዎች ጋር ሊወያዩ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከመላው ሀገሪቱ ከተውጣጡ የጤና ባለሙያዎች ጋር ሊወያዩ ነው ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ ከጤና ባለሙያዎች ጋር የሚያደርጉት ውይይትም የፊታችን ቅዳሜ ሚያዝያ 26 2011 ዓ.ም እንደሚካሄድ የጤና ሚኒስትር ዶክተር አሚር አማን  በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው አስፍረዋል። በጤና ባለሙያዎች ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደመወዝን […]

የጣና ፎረም ከአራት ቀናት በኋላ ይካሄዳል

የጣና ፎረም ከአራት ቀናት በኋላ ይካሄዳል 8ኛው የጣና ፎረም ” የፖለቲካ ሁኔታ ተለዋዋጭነት በአፍሪካ ቀንድ  “የሰላም ጅማሮዎችን ማስቀጠል “በሚል መሪ ቃል ሚያዝያ 25 እና 26 ቀን 2011 ዓም በባህርዳር ከተማ እንደሚካሄድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ። የዘንድሮው የጣና ፎረም በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል በቅርቡ የተደረሰውን የሰላም ስምምነት ተከትሎ የሚካሄድ በመሆኑ፤ የአፍሪካ የደህንነት ጉዳዮች ላይ በተለይም በአፍሪካ […]

በአማራ ክልል በተለያዩ ወቅቶች የሚከሰቱ የፀጥታ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት የሚያስችል ምክክር መጀመሩ ተነገረ

በአማራ ክልል በተለያዩ ወቅቶች የሚከሰቱ የፀጥታ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት የሚያስችል ምክክር መጀመሩ ተነገረ፡፡  በጉባኤው የተገኙት የኢፌዲሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ለችግሮች የሚመጥን የሕግ ማስከበር ሥራ እንዲኖር ለማስቻል ምክክሩ ለቀጣይ ስምሪቶች ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው ገልጸዋል፡፡ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሁሉም የክልሉ አከባቢዎች እና አጎራባች ስፍራዎች  የሕግ የበላይነት እንዲከበር እና ሕዝቡ የሚፈልገውን ሰላም ለማረጋገጥ የፌዴራል እና […]

በቅርቡ የተቋቋመው  የእርቀ ሰላም ኮሚሽን ለግጭቶች ዋነኛ መንስኤዎችን በማጥናት ዘላቂ ሰላም ለማምጣት እሰራለሁ አለ

በቅርቡ የተቋቋመው  የእርቀ ሰላም ኮሚሽን ለግጭቶች ዋነኛ መንስኤዎችን በማጥናት ዘላቂ ሰላም ለማምጣት እሰራለሁ አለ ፡፡ ኮሚሽኑ በቀጣይ ጊዜያት እውነትና ፍትህ ላይ መሰረት ያደረገ እርቅ ለማውረድ እንደሚሰራም ለጋዜጠኞች በሰጠው መግለጫ አስታውቋል፡፡ ኮሚሽኑ ወደ ስራ የገባው በኢትዮጵያ ለበርካታ ዓመታት ማህበረሰባዊና ፖለቲካዊ ምክንያት በህዝቦች መካከል የተደራረቡ የቁርሾ ስሜቶችን ለማከም እውነተኛና ፍትህን መሰረት ያደረገ እርቅ ማውረድ አስፈለጊ መሆኑን አምኖ […]

የ አይኤስ አይኤስ መሪው አልባግዳዲ አልሞትኩም እያለ ነው

ለአምስት አመታት ከእይታ ተሰውሮ የቆየውና በብዙዎች ዘንድ ሞቷል ተብሎ የታመነው የኢስላማዊ ታጣቂ (አይ ኤስ) ቡድን መሪ አቡ ባክር አልባግዳዲ በቅርቡ በለቀቀው  ተንቀሳቃሽ ምስል እንዳልሞተ አረጋግጧል። ከሁለት ሳምንት በፊት በስሪላንካ የፋሲካ በዓል ዕለት ለደረሰው የቦምብ ጥቃት ኃላፊነቱን ወስዷል። የኢስላማዊ ታጣቂ (አይ ኤስ) ቡድን መሪ አቡ ባክር አልባግዳዲ ድምጹን ካጠፋ ከአምስት ዓመታት በኋላ ነው ለመጀመሪያ ጊዜ በተንቀሳቃሽ […]