loading
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በዛሬው ዕለት ለአራት ከፍተኛ አመራሮች ሹመት ሰጡ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በዛሬው ዕለት ለአራት ከፍተኛ አመራሮች ሹመት ሰጡ። በዚሁ መሰረት  ቀድሞ የኦዲፓ ማዕከላዊ ጽህፈት ቤት ሃላፊ የነበሩትን ዶ/ር አለሙ ስሜን የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ቀድሞ የከተማ ልማት እና ኮንስትራክሽ ሚኒስትር የነበሩትን አቶ ጃንጥራር አባይን የጠቅላይ ሚኒስትሩ የመሰረተ ልማትና የከተማ ልማት አማካሪ ሚኒስትር ቀድሞ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ምክትል ርዕሰመስተዳድር […]

ጋህነን የትጥቅ ትግሉን ትቶ ወደሃገሩ ገባ

በኤርትራ የትጥቅ ትግል ሲያካሂድ የነበረው የጋምቤላ ህዝቦች ነፃነት ንቅናቄ በሰላማዊ መንገድ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ተሳታፊ ለመሆን ወደ ሀገሩ ገባ። የጋምቤላ ህዝቦች ነፃነት ንቅናቄ (ጋህነን) መቀመጫውን ኤርትራ በማድርግ የትጥቅ ትግል ሲያካሂድ ዓመታትን አስቆጥሯል። የንቅናቄው አባላትና አመራሮች ጋምቤላ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱም የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጁሉን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮችና ደጋፊዎቻቸው አቀባበል አድርገውላቸዋል። የንቅናቄው ሊቀመንበር አቶ ኡኬሎ […]

በሳዑዲ አረቢያ ያለመኖሪያ ፈቃድ ይኖሩ የነበሩ ኢትዮጵያዊያን ወደሃገራቸው ተመለሱ 

በሳዑዲ አረቢያ ያለመኖሪያ ፈቃድ ይኖሩ የነበሩ ኢትዮጵያዊያን ወደሃገራቸው ተመለሱ ። እነዚሁ 850 ኢትዮጵያውያን በሁለት ዙር ባሳለፍነው ሳምንት ወደ አገራቸው ተመልሰዋል። ከተመለሻቹ መካከል 445 ያህል ሰዎች ባሳለፍነው አርብ፣ ቀሪዎቹ 405 ደግሞ እሁድ እለት ወደሀገራቸው የገቡ ናቸው። ከስደት ተመላሾቹ ወደ ሀገራቸው የተመለሱት በራሳቸው ፈቃድ ሲሆን ሳዑዲ አረቢያ የገቡትም ቀይ ባህርን አቋርጠው በህገ-ወጥ መንገድ እንደነበር ተነግሯል። ተመላሾቹ ወደ ሀገራቸው […]

“ዘላቂ ሰላም የሚገኘው በህዝቡ ያላሳለሰ ጥረትና ትጋት እንዲሁም ከባለ ድርሻ አካላት ጋር በሚኖር መቀናጀት ነው” ዶ/ር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል

በትግራይ ክልል ዘላቂ ሰላም የሚገኘው በህዝቡ ያላሳለሰ ጥረትና ትጋት እንዲሁም ከባለ ድርሻ አካላት ጋር በሚኖር መቀናጀትና መደጋገፍ መሆኑን የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር  ዶክተር ደብረጺዮን ገብረሚካኤል አስገነዘቡ። በሰሜን እዝና በትግራይ ክልል ፀጥታና አስተዳደር ቢሮ የሰላምና የደህንነት ኮንፈረንስ ተካሂዷል። የትግራይ ክልል ፀጥታና አስተዳደር ቢሮ ከኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት የሰሜን እዝ አመራሮች ጋር የጋራ የሰላምና የደህንነት ኮንፈረንስ ባካሄዱበት […]

በሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር እና በሃይማኖት ተቋማት መካከል ስመምነት ተፈረመ

የሀይማኖት ተቋማት ለዜጎች በተናጥል የሚያደርጉትን ድጋፍ ውጤት በሚያመጣ መልኩ ለማቀናጀት የሚያስችል ነው የተባለ የመግባቢያ ስምምነት በሃይማኖት ተቋማትና በሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ተፈረመ። ሚኒስቴር መስሪያቤቱና  የሃይማኖት ተቋማት አረጋውያንን፣ አካል ጉዳተኞችን እና ለማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚነትና ተሳታፊነት ለማረጋገጥ የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ ጋር መፈራረማቸውን የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል። ስምምነቱ ለማህበራዊ እና […]

“ሃገሪቷ ያሏት ቅርሶች ብዛት ከእንክብካቤ እና እድሳት አቅም በላይ ነው” – ዶክተር ሂሩት ካሳው

በኢትዮጵያ ቅርሶችን ለመጠገን እና ለማደስ አስቸጋሪ የሆነው  ሃገሪቱ ያሏት ቅርሶች ብዛት ካላት የመንከባከብ  አቅም ጋር ስላልተመጣጠነ መሆኑን የባህል እና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶ/ር ሂሩት ካሳው ተናገሩ። ሚኒስትሯ ይህን ያሉት በአንድ አመት ጊዜ ውስጥ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የሚጠበቅበትን ሃላፊነት ለመወጣት ያደረገውን ጥረት እና የገጠሙትን ችግሮች በሚመለከት ለጋዜጠኞች መግለጫ በሰጡበት ወቅት ነው፡፡ ዶ/ር ሂሩት በመግለጫቸው በሀገራችን የቅርሶች ቁጥር […]