loading
የኢትዮጵያ ክለቦች አሁንም የባህር ማዶ ተጫዋቾችን ማስፈረማቸውን ቀጥለውበታል

የኢትዮጵያ ክለቦች አሁንም የባህር ማዶ ተጫዋቾችን ማስፈረማቸውን ቀጥለውበታል ዘንድሮ ከከፍተኛ ሊግ ወደ ፕሪምየር ሊጉ በድጋሜ የተመለሰው ደቡብ ፖሊስ በኢትዮጵያ ልምድ ያላቸውን ናይጄሪያዊያን አጥቂዎች ፊሊፕ ዳውዝ እና ላኪ ሳኒ አስፈርመዋል፡፡ ቡድኑ በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ሁሉንም የጨዋታ መርሀ ግብሮች አከናውኖ በአምስት ነጥቦች 15ኛ ላይ ተቀምጧል፡፡ በአንጋፋ ተጫዋቾች የተሞላውን ደቡብ ፖሊስ ከአጥቂ ችግሩ ለመላቀቅ የሊጉ የልምድ ባለቤቶች ፊሊፕ […]

ፕሬዚዳንት ሳህለ ወርቅ እርሳቸውን ተክተው ከተሾሙት በመንግታቱ ድርጅት የአፍሪካ ህብረት ልዩ ተወካይ ጋር መከሩ

ፕሬዚዳንት ሳህለ ወርቅ እርሳቸውን ተክተው ከተሾሙት በመንግታቱ ድርጅት የአፍሪካ ህብረት ልዩ ተወካይ ጋር መከሩ፡፡ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ በቅርቡ በተባበሩት መንግስታት ጽህፈት ቤት የአፍሪካ ህብረት ልዩ  ተወካይ ሆነው የተሾሙትን ሀና ሰርዋ በፅህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡ ልዩ ተወካይዋ ፕሬዝዳንት ሳህለ ወርቅን በመተካት የተሾሙ ሲሆን የጉብኝታቸው ዓላማም ለፕሬዝዳንቷ የእንኳን ደስ አለዎ መልዕክት ለማስተላለፍና በሌሎች ጉዳዮች ዙሪያ ለመምከር ነው ተብሏል። […]

አማራ ክልላዊ መንግስት በክልሉ የሚስተዋሉ የጸጥታ ችግሮች ታቅደው የሚደረጉ ሊሆኑ ይችላሉ የሚል ስጋት አለኝ አለ

የአማራ ክልላዊ መንግስት በክልሉ የሚስተዋሉ የጸጥታ ችግሮች ታቅደው የሚደረጉ ሊሆኑ ይችላሉ የሚል ስጋት አለኝ አለ የክልሉ መንግስት ይህን ያለው በክልሉ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በሰጠው መግለጫ ነው፡፡ የአማራ ክልል የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ አሰማኸኝ አስረስ በሰጡት መግለጫ በአብዛኞቹ የክልሉ አካባቢዎች የተሻለ ሰላም እና መረጋጋት ቢኖርም በአንዳንድ አካባቢዎች ግን የሰላም መደፍረስ ጎልቶ ይስተዋላል […]

ኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመች

ኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመች የውሃ መስኖ እና ኤሌክትሪክ ሚኒስቴር የመግባቢያ ሰነዱን  የተፈራረመው ገልፍ የኤሌክትሪክ ትስስር ከተባለ የባህረ ሰላጤው አባል ሀገራት  የኃይል አቀርቦት ተቋም እና የዓለም አቀፉ የኃይል ትስስር ድርጅት ጋር ነው፡፡ ሰነዱ የሃይል አቅርቦትን መሰረት ያደረገ ጥናት ለማካሄድ የሚያስችል  ነው ተብሏል፡፡ በፊርማ ስነ ስርዓቱ ላይም  የውሃ መስኖ እና ኤሌክትሪክ ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂነር […]

ሜጀር ጀነራል ክንፈ ዳኘውን ጨምሮ 14 የሜቴክ የቀድሞ ሰራተኞች ተጨማሪ ከስ ተመሰረተባቸው

ሜጀር ጀነራል ክንፈ ዳኘውን ጨምሮ 14 የሜቴክ የቀድሞ ሰራተኞች ተጨማሪ ከስ ተመሰረተባቸው፡፡ አቃቤ ህግ ግለሰቦቹ የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ከ28 ዓመታት በላይ የተገለገለባቸው አባይ ወንዝ እና አብዮት ከተባሉ ሁለት መርከቦች ግዢ ጋር በተያያዘ ተፈፅሟል ባላቸው የሙስና ወንጀሎች ነው የከሰሳቸው። ኮርፖሬሽኑ ምንም አይነት መርከብ የማስተዳደር ልምድ ሳይኖረው ሃላፊዎቹ ከሥልጣናቸው አልፈው  ተያያዥነት በሌለው ዘርፍ ለመሰማራት […]

ኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ የምርጫ ድምፅ ቆጠራውን በድጋሜ እንድታካሂድ ተጠየቀች

ኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ የምርጫ ድምፅ ቆጠራውን በድጋሜ እንድታካሂድ ተጠየቀች ኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ያካሄደችው ፕሬዚዳንታዊ የምርጫ ፉክክር የድምፅ ቆጠራ ውጤት ይፋ ቢደረግም፤ በተፎካካሪዎች ዘንድ የተሳሳተ ነው መባሉን ተከትሎ የደቡብ አፍሪካ ልማት ማህበረሰብ (ሳድክ)  የድምፅ ቆጠራውን በድጋሜ እንድታከናውን ጥሪ አቅርቦላታል፡፡ ኮንጎ ነፃነቷን ከተቀዳጀች ከ59 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ዴሞክራሲያዊ የስልጣን ሽግግር ማብሰሪያ  ይሆናል ብሎ ተስፋ የተጣበት ምርጫ […]

የኢራኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከጦርነት ይልቅ ጉርብትናችንን እናጠናክር እያሉ ነው

የኢራኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከጦርነት ይልቅ ጉርብትናችንን እናጠናክር እያሉ ነው የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መሀመድ ጃቫድ ዛሪፍ ጎረቤት ሀገራት ጠንካራ ወደጅነት መፍጠር የሚሹ ከሆነ፤ ከጦር መሳሪያ ክምችት ፉክክር ይልቅ ውይይትን ሊያስቀድሙ ይገባል ብለዋል፡፡ ዛሪፍ ይህን  ያሉት በኢራቅ መዲና ባግዳድ ለተሰባሰቡ በመቶዎች ለሚቆጠሩ የኢራን እና ኢራቅ የቢዝነስ ተቋማትን ወክለው ለተገኙ ግለሰቦች ነው፡፡ ጃቫድ ዛሪፍ በንግግራቸው ጠንካራ […]

በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ማንችስተር ሲቲ አሸንፏል

በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ማንችስተር ሲቲ አሸንፏል የ22ኛ ሳምንት መርሀግብር የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ የመጨረሻ ጨዋታ ትናንት ምሽት ኢቲሃድ ላይ በማንችስተር ሲቲ እና ወልቨርሃምፕተን ወንደረርስ መካከል ተካሂዷል፤ ወልቭስ ታላላቅ ክለቦችን ሲገጥም የሚያሳየውን ፉክክር ተከትሎ የምሽቱን ጨዋታ ተጠባቂ አድርጎት ነበር፡፡ በምሽቱ በተደረገው ግጥሚያ የፔፕ ጓርዲዮላው ሲቲ የ3 ለ 0 ድል በወልቭስ ላይ ተቀዳጅቷል፡፡ ድሉን ተከትሎ ከሊቨርፑል ጋር ያለውን […]

በቡራዩ  ከተማ  የእሳት አደጋ በንብረ ትላይ  ጉዳት አደረሰ፡፡

በቡራዩ  ከተማ  የእሳት አደጋ በንብረ ትላይ  ጉዳት አደረሰ፡፡ በቡራዩ ከተማ ለኩ ኩሌ ቀበሌ ከሌሊቱ 8 ሰአት ከሰላሳ ላይ ኢንተማ ትሬዲንግ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ሻማ የሚያመርት ፋብሪካ ላይ በደረሰ የእሳት አደጋ ፋብሪካው ሙሉ ለሙሉ ወድሟል፡፡ የቡራዩ  ከተማ ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር መርጊያ ሁንዴሳ ለአርትስ ቴሌቭዥን  እንደተናገሩት በእሳት አደጋው  ከፋብሪካው አቅራቢያ የሚገኙ ሁለት  ሱቆች ተቃጥለዋል፡፡ በቃጠሎ አደጋው […]

ኢትዮጵያዊያን አምባሳደሮች አመታዊ  ጉባኤያቸውን እያካሄዱ ነው ፡፡

ኢትዮጵያዊያን አምባሳደሮች አመታዊ  ጉባኤያቸውን እያካሄዱ ነው ፡፡ ኢትዮጵያን በውጭ የሚወክሉ አምባሳደሮች ቆንስላ ጄኔራሎች እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዳይሬክተር ጄኔራሎች የሚሳተፉበት ጉባኤ ለአንድ ሳምንት የሚቆይ ነው፡፡ ጉባኤው  በዋናነት የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት  እና በውጭ የሚገኙ ሚሲዮኖች የስራ እንቅስቃሴ ፣የሚያጋጥሙ  ችግሮች እና መፍትሄዎቸቻው ላይ ያተኩራል ተብሏል፡፡ ሌላው የውይይቱ አጀንዳ ክልላዊ እና ዓለምአቀፋዊ ጉዳዮች በኢትዮጵያ እና በጎረቤት አገራት […]