loading
በኢትዮጵያ የእንግሊዝ ኢምባሲ የመጀመርያ ዲግሪ ላላቸው ኢትዮጵያውያን ነፃ ትምህርት ዕድል ሊሰጥ ነው፡፡

በኢትዮጵያ የእንግሊዝ ኢምባሲ የመጀመርያ ዲግሪ ላላቸው ኢትዮጵያውያን ነፃ ትምህርት ዕድል ሊሰጥ ነው፡፡ በኢትዮጵያ የእንግሊዝ ኤምባሲ የመጀመርያ ዲግሪ ላላቸው ኢትዮጵያውን ነጻ የትምህርት ዕድል እንደሚሰጥ በኢትዮጵያ የእንግሊዝ ኢምባሲ ከፍተኛ የፖለቲካ ባለሙያ ጀሚ ኦርተን ገልጸዋል፡፡ ጀሚ ኦርተን ከአማራ ብዙኃን መገናኛ ጋር ባደረጉት ቆይታ የእድሉ ተጠቃሚ የሚሆኑት ተማሪዎች በማንኛውም የትምህርት ዘርፍ የመጀመርያ ዲግሪ ያላቸው አምልካቾች መሆኑን አስታውቀዋል፡፡ አመልካቾች ሁለት […]

በሀገር ደረጃ የሚሰራ የፎረንሲክ ማዕከል ባለመኖሩ አስቸኳይ ዉሳኔ የሚያስፈልጋቸዉን ጉዳዮች ቶሎ መርምሮ ለማወቅ እንቅፋት እየሆነ ነዉ ፡፡

በቅዱስ ጳዉሎስ ሆስፒታል የፎረንሲክ ሜዲስን ቴክኖሎጂ ሃላፊ ዶክተር እንየዉ ደባሽ ለአርትስ ቲቪ እንደተናገሩት የቅዱስ ጳዉሎስ ሆስፒታል የአስክሬን ምርመራ ፤የእድሜና የፆታ ጥቃት ሲደርስ በፎረንሲክ ክፍሉ ምርመራ ቢያደርግም፤ ከአባትነትና ከእናትነት ማረጋገጫ መሰል ዝርዝር የምረዛ ችግሮች ሲኖሩ ከሀገር ዉጪ ናሙና በመላክ ምርመራ ይደረጋል ብለዋል፡፡ በፎረንሲክ ምርመራ ባለሞያዎችን ወደ ህንድ በመላክ ለማሰልጠን ቢቻልም አገልግሎቱን በተገቢና በተቀላጠፈ መልኩ ለመስጠት መመርመሪያ […]

የአሜሪካ ኮንግረስ አዲስ ታሪክ አስመዝግቧል፡፡ ምክር ቤቱ የመጀመሪያዋን ሙስሊም ሴት ተወካይ በማስመረጡ ነው አዲስ ታሪክ ተብሎ የተመዘገበለት፡፡

የአሜሪካ ኮንግረስ አዲስ ታሪክ አስመዝግቧል፡፡ ምክር ቤቱ የመጀመሪያዋን ሙስሊም ሴት ተወካይ በማስመረጡ ነው አዲስ ታሪክ ተብሎ የተመዘገበለት፡፡ አልጀዚራ እንደዘገበው ረሽዳ ጣሊብ የተባሉት ሴትም የዚህ አዲስ ታሪክ ባለቤት ለመሆን በቅተዋል፡፡ ጣሊብ ለምክር ቤት ወንበር ተወዳድረው አሸናፊ ለመሆን የበቁት በሚሽጋን ግዛት ነው ፡፡ የ42 ዓመቷ ወይዘሮ የዴሞክራቲክ ፓርቲ ተወካይ ሲሆኑ ተፎካካሪቸው ሆነው የቀረቡትን ብሬዳ ንጆንሰንን 33.6 በ28.5 […]

በጅግጅጋ ከተማ የተጎዱ ወገኖችን ለመርዳት የተላከው የጤና ባለሙያዎች ቡድን ትላንት ሀምሳ ዘጠኝ ለሚደርሱ ተጎጂዎች የህክምና እርዳታ አደረገ፡፡

ከታካሚዎች ዉስጥም ሰላሳ የሚሆኑት ቀዶ ጥገና የሚያስፈልጋቸው ናቸው ። ከነዚህ ዉስጥም ዘጠኝ ለሚሆኑ ተጎጂዎች ቀዶ ጥገና የተደረገ ሲሆን የተቀሩት በዛሬ እለት የቀዶ ጥገና ህክምና እርዳታ ይደረግላቸዋል ተብሏል። የጤና ጥበቃ ሚኒስትሩ ዶክተር አሚር አማን ለጤና ባለሙያዎቹ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

በኤሌክትሪክ ኃይል ታሪፍ ላይ ጭማሪ ሊደረግ ነው::

በኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚዎች ላይ የታሪፍ ጭማሪ ለማድረግ አስፈላጊው ሂደት መጀመሩን የኢትዮጵያ ኢነርጂ ባለስልጣን አስታወቀ፡፡ ማሻሻያው ዝቅተኛ የኃይል ተጠቃሚዎችን አያካትትም ተብሏል፡ ቢቢሲ የኢትዮጵያ ኢነርጂ ባለስልጣን ዳይሬክተር የሆኑትን አቶ ጌታሁን ሞገስን አናግሮ እንደዘገበዉ የኤሌክትሪክ ታሪፍ ጭማሪው በተለያዩ ደረጃዎች አልፎ ተቀባይነት ሲያገኝ ተግባራዊ እንደሚሆን ተናግረዋል። አቶ ጌታሁን የታሪፍ ጭማሪ ማድረግ ያስፈለገበትን ምክንያት ለመጨረሻ ጊዜ የታሪፍ ጭማሪ ተደርጎ […]

የኢንጅነር ስመኘው በቀለን ቤተሰቦችን ለመደገፍ የገቢ አሰባሳቢ ኮሚቴ ተዋቅሯል::

በሀይደሮ ፓወር ዙሪያ የሚያጠኑና ከፍተኛ ዉጤት ለሚያገኙ ተማሪዎች ኢንጅነር ስመኘዉ በቀለ አዋርድ በሚል ለመስጠት እቅድ ተይዟል ተባለ፡፡ የኢንጅነር ስመኘው በቀለን ቤተሰቦችን ለመደገፍ የገቢ አሰባሳቢ ኮሚቴ ተዋቅሯል:: የመንግስት ኮሙኒኬሽን በድረገጹ እንዳስታወቀዉ ሐምሌ 19 ቀን 2010 ዓ.ም በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ በመኪናቸው ውስጥ ህይወታቸው አልፎ የተገኙትን የኢንጅነር ስመኘው በቀለን ቤተሰቦች መደገፍ የሚያስችል የገቢ አሰባሳቢ ኮሚቴ ተዋቅሯል። ኮሚቴው […]

ኢንዶኔዥያ ዳግም በከባድ ርዕደ መሬት ተመታች፡፡

ኢንዶኔዥያ ዳግም በከባድ ርዕደ መሬት ተመታች፡፡ በዛሬዉ ዕለት ኢንዶኖዥያ ሎምቦክ ደሴት አካባቢ በደረሰ ከባድ የመሬት መንቀጥቀጥ በርካታ ቤቶች ፈራርሰዋል፡፡ነዋሪዎችም አካባቢቸዉን ጥለዉ ሸሽተዋል፡፡ በርዕደ መሬቱ መለኪያ 6.2 እንዲሁም 6.9 የሆነ ተከታታይ የመሬት መንቀጥቀጥ በተከሰተባት ኢንዶኔዥያ 156 ሺህ ዜጎች ቤት አልባ ሆነዋል፡፡ አልጀዚራ እንደዘገበዉ እስካሁን በአደጋዉ ሳቢያ 131 ሰዎች ህይወታቸዉን አጥተዋል፡፡ከሟቾቹ በተጨማሪ ከ1ሺህ 400 በላይ ሰዎች ከባድ […]

በቀጥታ የዘር ግብይት ሥርዓት ከ 1 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ ማዳን ተቻለ፡፡

የኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሚሽን ኤጀንሲ ከግብርና እንስሳት ሃብት ሚኒስቴር ጋር በጋራ በመሆን የቀጥታ የዘር ግብይት ሥርዓትን በተመለከተ ውይይት አካሂዷል፡፡ የቀጥታ የዘር ግብይት ስርዓት በማስረጽ ከዚህ በፊት በዘር አከፋፋይ እና በአርሶ አደሩ ይደርስ የነበረውን ችግር እና ውጣውረድ በማስቀረት ዘር አምራቹን ከአርሶ አደሩ ጋር በቀጥታ በማገናኝት ይባክን የነበረውን የሰው ጉልበት እና ሃብት ማስቀረት ተችሏል፡፡ የግብርናና አንስሳት ሃብት ሚኒስቴር […]

ሊቨርፑሎች ዓመቱ የኛ ነው እያሉ ነው።

የሊቨርፑል ደጋፊዎች ክለባቸው የፕሪሚየር ሊጉን ዋንጫ ካነሳ ሃያ ስምንት ዓመታትን ያስቆጠረ ቢሆንም መጭው ዘመን የኛ ነው በማለት ሊጉ ከመጀመሩ በፊት እየፎከሩ ነው ይላል የ ዘሰን ዘገባ። ይህን ተከትሎም የርገን ክሎፕ ከአምናው ሻምፒዮን ጋርዲዮላ በልጠው ለመገኘት ከአሁኑ ትልቅ የቤት ስራ ይጠብቃቸዋል። ክሎፕ አስተያየታቸውን ሲሰጡም ማንቸተር ሲቲዎች የትኛውንም ክለብ የማሸነፍ ብቃት አላቸው፤ ቢሆንም ግን ከረጅም ጊዜ በኋላ […]