loading
ከኢህአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ

የኢህአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ከነሀሴ 14 እስከ 16/2010 ዓ.ም ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ የጥልቅ ተሃድሶውን አፈፃፀምና ያስገኘውን ውጤት በተለመደው ድርጅታዊ ባህል፣ ዴሞክራሲያዊነትን በተላበሰ እና በሰከነ አግባብ በጥልቀት ገምግሟል፡፡ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴው የጥልቅ ተሃድሶውን ተከትሎ የተወሰዱ የለውጥ እርምጃዎች የአመራር ፈጠራ ታክሎባቸው የለውጡ ቱርፋት የሆኑ አመርቂ ውጤቶች መመዝገባቸውን አረጋግጧል፡፡ ከአሁን በፊት ውሳኔዎች እየተወሰኑ እና አቅጣጫዎች እየተቀመጡ በአፈፃፀም ድክመት ይታይባቸው […]

የዘንድሮው የአሸንዳ በአል በመቀሌ ከተማ ስታዲየም “አሸንዳ ለሰላም እና አንድነታችን” በሚል መሪ ቃል ተከብሮ ውሏል፡፡

በክብረ በዓሉ የመንግስተ አመራሮች፣ የኪነጥበብ ባለሞያዎች እንዲሁም በርካታ ቁጥር ያላቸአው ታዳሚዎች ተገኘተውበታል፡ የባህል እና ቱሪዝም ሚኒስቴር ወ/ሮ ሶፊያ አሚን የህዝቦች አንድነት፣መፈቃቀር፣አብሮ የመኖር ትስስርን ከሚያጠናክሩ ጠቃሚ እሴቶች እና ክብረ በአላት መሃከል አሸንዳ አንዱ እንደሆነ ገልፀው እነዚህ እሴቶች የሰላም እና አንድነት ማገር ሆነው ከትውልድ ትውልድ ይተላለፉ ዘንድ ጠንክረን መስራት አለብን ብለዋል፡፡ የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ደ/ር […]

የአፍሪካና የቻይና ግንኙነት ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሷል ተባለ፡፡

ሮይተርስ እንዘገበው በቻይናና በአፍሪካ መካከል ያለው የንግድ ልውውጥ መጠን እስካለፈው ዓመት ድረስ 170 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ደርሷል፡፡ በመጭው መስከረም ወር ላይ  የቻይና አፍሪካ የትብብር ፎረም  ቻይና ውስጥ ይካዳል፡፡ ፎረሙም በቻይናና በአፍሪካ መካከል ያለውን ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር ትልቅ ሚና ይኖረዋል ተብሏል፡፡ ቻይና ለአፍሪካ ሀገራት ለአቅም ግንባታ የሚውል 10 ቢሊዮን ዶላር የድጋፍ ገንዘብ መድባለች፡፡ ገንዘቡ […]

ብ/ጀነራል አሳምነው ፅጌ እና ብ/ጀነራል ተፈራ ማሞ በላሊላ አሸንድዬ ካባ ተደረበላቸው።

አሸንድዬ፣አሸንዳ ፣ሶለል እና ሻደይ የዓለም ሀብት የሚሆኑት በባለቤትነት ስንጠብቃቸው ነው ብለዋል የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትሯ ወ/ሮ ፎዚያ አሚን። የአሸንድዬ የሴቶች በዓል “አሸንድዬ ለሰላምና አንድነት በፍቅር ለመደመር” በሚል መሪ ቃል በላሊበላ ከተማ በድምቀት እየተከበረ ነው። በበዓሉ ላይ ብ/ጀነራል አሳምነው ፅጌ ወጣቶች ለሰላም ስሩ ሲሉ ብ/ጀነራል ተፈራ ማሞ ደግሞ ባህል የሚታወቀው አገር ሲኖር ነው ብለዋል ። አርትስ ቲቪ […]

ኢንጂነር ታከለ ኡማ በኮየ ፈጬ ሳይት የሚገኙ የጋራ መኖሪያ ቤቶች የሚገኙበትን ደረጃ ጎበኙ

በምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ የተመራውና የከተማ አስተዳደሩ የስራ ኃላፊዎችን ያካተተ ልኡካን በ11ኛው ዙር የተላለፉ የኮዬ ፈጬ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ውስጥ የሚገኙ ነዋሪዎችን አነጋግረዋል። ነዋሪዎች የተለያዩ መሰረተ ልማቶች ባለማሟላቱ ቅሬታቸውን ገልጸውላቸዋል በተለይም የውሃ፣ የመብራት  እና የባለድርሻ አካላት በቅንጅት ተናበው አለመስራት በኑሮአቸው ላይ ተጽዕኖ እንደፈጠረ ነው የገለጹት፡፡ ከንቲባ ኢንጂነር ታከለም የሚመለከታቸው የስራ ኃላፊዎች የህብረተሰቡን ቅሬታ ወስደው […]

የአሜሪካ መንግስት ልኡካን በኢትዮጵያ ጉብኝት ለማድረግ በዛሬው እለት አዲስ አበባ ይገባሉ።

በሪፐብሊካን ኮንግረስማን ክሪስቶፈር ስሚዝ የሚመራው የልኡካን ቡድን በኢትዮጵያ እየመጡ ባሉ ለውጦች ዙሪያ ከኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አበይ አህመድ እና ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ ጋር ተገናኝተው እንደሚወያይም ይጠበቃል። የልኡኩ መሪ ኮንግረስማን ክርስቶፈር ስሚዝ ከአሜሪካ ድምፅ (ቪኦኤ) ራዲዮ ጋር ባደረጉት ቆይታ፥ በኢትዮጵያ በሚኖራቸው ቆይታ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ እና ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወረቅነህ ጋር […]

የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ አገልግሎት ለመስጠት እየሰራ ነው አለ፡፡

ተቋሙ ባለፉት አመታት ለፓርቲ የወገነ አሰራር መተግበሩና ከተሰጠው አገራዊ ተልእኮ ውጪ ዜጎችን የማፈን የማሰርና ኢሰብአዊ ምርመራ ሲያደርግ መቆየቱ ተቋሙ እንዲፈራ አድርጎት ቆይቷል ተብሏል፡፡ የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ጀነራል አደም መሀመድ ከኢቢሲ ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደተናገሩት ከተቋሙ አሰራር ጋር በተያያዘ የሚነሱ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታትም ተቋሙ የተቋቋመበትን አዋጅ ማሻሻልን ጨምሮ የሪፎርም ስራዎችን እያከናወነ ነው ፡፡ በተቋማዊ የሪፎርም ስራው […]

ባለፈው ሰኔ በአሶሳ በተከሰተው የፀጥታ ችግር ጉዳት የደረሰባቸው ወገኖች ድጋፍ ለማድረግ መወሰኑን የክልሉ መንግስት አስታወቀ፡፡

ያን ግዜ በተከሰተው የፀጥታ ችግር ህይወታቸውን ላጡና ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ከ2 ሚሊዮን ብር በላይ ለድጋፍ አጽድቋል፡፡ የቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል መንግስት በግጭቱ ምክንያት ህይወታቸው ላለፈ 16 ግለሰቦች ቤተሰብ ለእያንዳንዳቸው 30 ሺ ብር፣ በግጭቱ ምክንያት ከባድ የአካል ጉዳት ለደረሰባቸው 11 ግለሰቦች ለእያንዳንዳቸው 20ሺ ብር እንዲሁም በግጭቱ ምክንያት ቀላል ጉዳት ለደረሰባቸው 78 ግለሰቦች ደግሞ ለእያንዳንዳቸው 10 ሺ ብር […]

የአሜሪካና የቻይና የንግድ ጦርነት ተባብሷል፡፡

ሲጂቲኤን እንደዘገበው ሁለቱ ሀገሮች ብድር እየተመላለሱ አንዱ በሌላው ላይ የታሪፍ ጭማሪ መቀጠሉን ተያይዘውታል፡፡ አሁን አሜሪካ በቻይና ምርቶች ላይ የ25 በመቶ የታሪፍ ጭማሪ መጣሏን ተከትሎ ቻይናም በብርሃን ፍጥነት በዋሽንግተን ምርቶች ላይ ተመሳሳይ ታሪፍ ጥላባቸዋለች፡፡ አሜሪካ የ25 በመቶ ታሪፍ የጣለችው ከቻይና ወደ ሀገሯ በሚገቡ የኤሌክትሮኒክስ፣ የፕላስቲክ፣ የባቡር መገጣጠሚያ መሳሪያዎችና የኬሚካል ውጤቶች ላይ ሲሆን ቻይና በአጸፋው በተሸከርካሪዎች፣ በኢነርጂና […]