loading
የመጀመሪያው የቴክኖሎጂ ከተማ በባህር ዳር ሊገነባ ነው፡፡

የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስትና ከአሜሪካው ሀብ ሲቲ ላይቭ ፕሮጀክት ጋር በመተባበር በባህር ዳር ከተማ የመጀመሪያውን የቴክኖሎጂ ከተማ (Technology Hub City) ለመገንባት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ የምክክር መድረክ አዘጋጅቷል፡፡ የምክክር መድረኩ በሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ነገ ይካሄዳል፡፡ ምክክሩ Ethiopia is the Real WAKANDA በሚል ርዕስ እንደሚካሄድ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በገፁ ፅፏል፡፡ የቴክኖሎጂ ከተማው በከፍተኛ ወጪ […]

ለስደተኞች ስራ በማትሰጠው ለንደን ወጣቱ ሲቪውን ይዞ ጎዳና ላይ ለመቆም ተገዷል ፡፡

ሞሀመድ ኤልባራዲ ይባላል፡፡ የ22 ዓመት ወጣት ነው፡፡ ከሊቢያ ተሰዶ መኖሪያውን ለንደን ያደረገው ኤልባራዲ ከለንደን ዩንቨርሲቲ ኮሌጅ በኤሮስፔስ ሳይንስ በማስተርስ ዲግሪ ተመርቋል፡፡ ሆኖም ከ70 በላይ በሚሆኑ ቀጣሪ ድርጅቶች ውስጥ የስራ ማመልከቻ ቢያስገባም አንዳቸውም ምላሽ አልሰጡትም፡፡ በዚህ ሁኔታ የተማረረው ኤልባራዲ ታዲያ በመጨረሻ አንድ ሀሳብ መጣለት፡፡ ስራ እንደሚፈልግ የሚጠቁም ማስታወቂያ ይዞ ሰው በሚበዛበት አካባቢ መቆም፡፡ እናም ይህ ወጣት […]

በህንድ በተከሰተ የጎርፍ አደጋ ከመቶ በላይ ሰዎች ሲሞቱ በሺዎች ሚቆጠሩት ደግሞ ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለዋል ፡፡

በህንድ በተከሰተ የጎርፍ አደጋ ከመቶ በላይ ሰዎች ሲሞቱ በሺዎች ሚቆጠሩት ደግሞ ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለዋል ፡፡ ቢቢሲ እንደዘገበው የህንዷ ኬራላ ግዛት ህንድን በክፍለ ዘመኑ ካጋጠማት አስከፊውን የጎርፍ አደጋ አስተናግዳለች፡፡ የግዛቷ ባለስልጣናት እንደተናገሩት በአደጋው ሳቢያ 164 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል፡፡ ከሟቾቹ በተጨማሪም ቁጥራቸው ወደ 23 ሺህ የሚጠጋ ነዋሪዎች ቤት አልባ ሆነዋል፡፡ ባለስልጣናቱ ነዋሪዎቹ በፍጥነት የአደጋውን አካባቢ ለቀው እንዲወጡም […]

አዲስ አመትን ለማክበር ወደ አዲስ አበባ እየገቡ ያሉ በውጪ ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በበጎ ፍቃድ አገልግሎት ለመሳተፍ ጥያቄ ማቅረባቸዉን የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ በትዊተር ገጻቸዉ አስታዉቀዋል፡፡

አዲስ አመትን ለማክበር ወደ አዲስ አበባ እየገቡ ያሉ በውጪ ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በበጎ ፍቃድ አገልግሎት ለመሳተፍ ጥያቄ ማቅረባቸዉን የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ በትዊተር ገጻቸዉ አስታዉቀዋል፡፡ ኢንጂነር ታከለ ዲያስፖራውን በቀጣይም በከተማዋ ልማት ላይ እንዲሳተፍ ጥሪያችንን እናቀርባለን ብለዋል

ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በበርሚንግሃም ዳይመንድ ሊግ በነገው ዕለት ከሰአት በኋላ በተለያዩ ሩጫዎች ይካፈላሉ፡፡

ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በበርሚንግሃም ዳይመንድ ሊግ በነገው ዕለት ከሰአት በኋላ በተለያዩ ሩጫዎች ይካፈላሉ፡፡ በሴቶች 1500 ሜ በ10:22 ሰዓት፤ አክሱማይት እምባዬ ጉዳፍ ፀጋዬ አልማዝ ሳሙኤል በወንዶች 3000 ሜ መሰናክል በ10:33 ሰዓት፤ ጫላ ባዮ በሴቶች 3000 ሜ. በ10:49 ሰዓት፤ እጅጋየሁ ታዬ

ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ቁጥሩ በውል ያልታወቀ የጦር መሳሪያ በቁጥጥር ስር ማዋሉን ገለጸ፡፡

ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ቁጥሩ በውል ያልታወቀ የጦር መሳሪያ በቁጥጥር ስር ማዋሉን ገለጸ፡፡ ኢቢሲ እንደዘገበዉ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ቁጥሩ በውል ያልታወቀ በነዳጅ ቦቴ ሲዘዋወር የነበረ የጦር መሳሪያ በቁጥጥር ስር አውሏል፡፡ በዚህም 1051 ሽጉጦች፣ መጠናቸው ያልታወቁ ጥይቶች እና ወደ ውጪ ሊወጣ የነበር መጠኑ ያልታወቀ ገንዘብ ቁጥጥር ስር መዋሉን የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ገልጿል፡፡

ሳልቫ ኪር ኤርትራን ሊጎበኙ ነው፡፡

ሳልቫ ኪር ኤርትራን ሊጎበኙ ነው፡፡ የኤርትራ ፕሬስ እንደዘገበው የደቡብ ሱዳኑ ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር አስመራን የመጎብኘት እቅድ ይዘዋል፡፡ የሁለቱ ሀገራት መሪዎች ለመጨረሻ ጊዜ የተገናኙት ደቡብ ሱዳን ራሷን ችላ ሀገር መሆኗን በይፋ ስታውጅ ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ ጁባ በተገኙበት ወቅት ነበር፡፡

ለአዲስ ዓመት ከውጪ ሀገር ለሚመጡ ኢትዮጵያዉያን ዲያስፖራዎች 25 በመቶ የጤና አገልግሎት ቅናሽ ይደረግላቸዋል ተባለ፡፡

ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር በሰው መግለጫ ከ ነሃሴ 14 ቀን 2010 ዓ.ም ጀምሮ የሚመጡ ኢትዮጲያዉያን ዲያስፖራዎች የአገልግሎት ቅናሹ ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ተነግሯል፡፡ በጤና ጥበቃ ሚንስቴር የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶክተር ተገኔ ረጋሳ በፌደራል እንዲሁም በክልል የጤናውን ዘርፍ በተመለከተ ለሚመጡት ዲያስፖራዎች መረጃ እንዲሰጥ የተዋቀረ የድንገተኛ አስተባባሪ ቡድን መዘጋጀቱን ተናግረዋል፡፡ ዜጎች ወደ ሃገር ቤት ሲመጡ ከሚያገኙት የጤና አገልግሎት ባሻገር […]