1መቶ 80 ሺህ የአሜሪካ ዶላርን ጨምሮ የ3 ሀገራት የዉጭ ገንዘብ በህገወጥ መንገድ ከሀገር ሊወጣ ሲል ተያዘ፡፡
1መቶ 80 ሺህ የአሜሪካ ዶላርን ጨምሮ የ3 ሀገራት የዉጭ ገንዘብ በህገወጥ መንገድ ከሀገር ሊወጣ ሲል ተያዘ፡፡
በቶጎ ጫሌ የፍተሻ ጣቢያ የተያዘ ገንዘብ ወደ ብር ሲቀየር ከ8 ሚሊዮን ብር በላይ እንደሆነ ገቢዎች ሚኒስቴር ገልጿል፡፡
በዛሬዉ ዕለት ኮድ 3 04867 ድሬ የሆነ ተሽከርካሪ ከሌሊቱ 11 ሰዓት ላይ በቶጎ ጫሌ ኬላ 182 ሺህ 247 የአሜሪካን ዶላር ወደ ኢትዮጵያ ብር ሲቀየር አምስት ሚሊዮን ሁለት መቶ ሰማኒያ አምስት ሺ አንድ መቶ ስልሳ ሶስት ብር ፤እና ሌሎች ሀገራት ገንዘብ ጨምሮ በድምሩ በእለቱ ምንዛሪ 8 ሚሊዮን ብር በላይ ገንዘብ ከሀገር ሊወጣ ሲል ተይዟል፡፡
ገንዘቡን ሲያዘዋውሩ የነበሩ ሁለት ግለሰቦችም በቁጥጥር ስር ዉለዋል፡፡
የገቢዎች ሚኒስትር ወ/ሮ አዳነች አቤቤ የግል ጥቅማቸዉ ሳያስቀድሙ እና የኮንትሮባዲስቶች ድለላ ሳይበግራቸዉ ለሀገራቸው ሌት ተቀን እየሰሩ ለሚገኙት የቶጎጫሌ ጉሙሩክ ሰራተኞች እና አመራሮች አድናቆታቸዉን መግለጻቸዉን ከሚኒስቴሩ ያገኘነዉ መረጃ ያመለክታል፡፡