loading
ፖል ፖግባ 500 ሺ ፓውንድ ሳምንታዊ ደሞዝ እንዲከፈለው ይፈልጋል ተባለ

የማንችስተር ዩናይትዱ የ26 ዓመት ፈረንሳያዊ አማካይ ፖል ፖግባ ፤ ስሙ ከተለያዩ ክለቦች ጋር ተያይዞ ቢነሳም ከሪያል ማድሪድ ጋር ያለው የዝውውር ወሬ ግን በሰፊው እየተነገረለት ይገኛል፡፡

እንደ ዘ ሰን ዘገባ ተጫዋቹ ከክለቦች የሚመጣለትን የእናስፈርምህ ጥያቄ ችላ ብሎ፤ በኦልድ ትራፎርድ ለመቆየት አምስት መቶ ሺ ፓውንድ በሳምንት እንዲከፈለው እንደሚፈልግ ዘግቧል፡፡

ፖግባ ከቀያይ ሰይጣኖቹ ጋር ያለው ውል ገና ሁለት ዓመት የሚቀረው ቢሆንም ዚነዲን ዚዳን በተጫዋቹ ላይ ያለው ፍላጎት ከፍ እያለ መምጣቱን ተከትሎ፤ ማንችስተር ዩናይትድ ከፖግባ ጋር መነጋገር እንደሚፈልግ እየተነገረ ይገኛል፡፡

ፈረንሳያዊው ተጫዋች በሳምንታዊ ክፍያ ከዩናይትድ ከፍተኛ ተከፋይ አሌክሲስ ሳንቼዝ ጋር መስተካከል ይፈልጋል፡፡

ዩናይትድ ተጫዋቹን አሁን ካለው የሁለት ዓመት ውል በተጨማሪ እስከ 2024 ድረስ ውሉን እንዲያራዝም ወረቀት እና ብዕር ጠረቄዛ ላይ የማቅረብ ፍላጎት አለው ተብሏል፡፡

ፖል ፖግባ አሁን ላይ በሳምንት የ300 ሺ ፓውንድ ሳምንታዊ ክፍያ ይፈፀምለታል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *