loading
ፖል ቢያ ከእንገንጠል ባዮች ጋር ለመወያየት ዝግጁ ነኝ አሉ

የካሜሮኑ ፕሬዝዳንት ፖል ቢያ እንግሊዘኛ ተናጋሪዎችን ፈረንሳይኛ ከሚናገሩት ለመገንጠል ከሚታገሉት ሚሊሻዎች ጋር ስለሰላም ለመወያየት እቅድ እንዳላቸው ተናግረዋል፡፡

ፕሬዝዳንቱ ለሰላም ልቡንም በሩንም ክፍት ለማድረግ ፈቃደኛ ከሆነ ማንኛውም ወገን ጋር ለመደራደርና መፍትሄ ለማፈላለግ ምንጊዜም ዝግጁ ነኝ ብለዋል፡፡

ፕሬዝዳንቱ አዲሱን ዓመት አስመልክተው ባደረጉት ንግግር ይህን ስል ጦርነትን እንደጀብድ የሚቆጥሩት እና የሰላም ጥሪያችንን የማያከብሩትን የመከላከያ ሀይላችን ልክ ሲያስገባቸው እንደሚችል መዘንጋት የለበትም ብለዋል፡፡

አፍሪካ ኒውስ እንደዘገበው ፕሬዝዳንት ፖል ቢያ ከተገንጣዮቹ ጋር በሰላም ለመወያየት ማሰባቸውን ይፋ ሲያደርጉ ይህ የመጀመሪያቸው ነው፡፡

አንግሎፎን በመባል የሚታወቀውን እንግሊዘኛ ተናጋሪዎች የሚበዙበትን አካባቢ ለመገንጠል የሚንቀሳቀሱት የሚሊሻ አባላት መሪዎች አብዛኞቹ በአሸባሪነት ተከሰው ጉዳዮቻቸው በወታደራዊ ፍርድ ቤት እየታየ ይገኛል፡፡

በአሁኑ ጊዜ  በሰሜን እና ደቡብ ምእራብ የሀገሪቱ ክፍሎች በተፈጠረው ግጭት  ሳቢያ በርካታ ካሜሮናዊያን ህይወታቸው ሲያልፍ ብዙዎቹ ደግሞ ወደ ጎረቤት ናይጀሪያ ተሰደው ይኖራሉ፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *