loading
ፖሊስ በቡራዩና አካባቢው በተፈፀመው የሽብር ወንጀል ተጠርጥረው በተያዙ 32 ግለሰቦች በ15 ሺ ብር ዋስትና እንዲወጡ ፈቀደ

ፖሊስ በቡራዩና አካባቢው በተፈፀመው የሽብር ወንጀል ተጠርጥረው በተያዙ 32 ግለሰቦች በ15 ሺ ብር ዋስትና እንዲወጡ ፈቀደ

አርትስ 05/04/2011

የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ የወንጀል ችሎት በዛሬ ውሎው በቡራዩ እና አካባቢው በተፈፀመው የሽብር ወንጀል ተጠርጥረው የተያዙ 33 ግለሰቦችን ጉዳይ ተመልክቷል።
ፍርድ ቤቱ ከዚህ ቀደም መርማሪ ፖሊስ በተጠርጣሪዎች ላይ ያቀረበው የሰውና የሰነድ ማስረጃ ለዐቃቤ ህግ ቀርቦ ተገቢነቱ እንዲጣራ መጠየቁ ይታወሳል።ይሁን እንጂ መርማሪ ፖሊስ በወቅቱ ጉዳት የደረሰባቸውን ሰዎች የሙሉ ምስክርነት ቃል ለመቀበል እንዲሁም ተጎጅዎችን በአካል ማነጋገር አስፈላጊ መሆኑን ለፍርድ ቤቱ በማስረዳት 28 ቀን ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ እንዲፈቀድለት ጠይቋል።
የተጠርጣሪ ጠበቆች በበኩላቸው ባለፈው ችሎት መርማሪ ፖሊስ ጉዳዩን አጣርቶ ለዐቃቤ ህግ እንዲያቀርብ ቢያዝም ፖሊስ ግን ይህን ማስፈፀም አለመቻሉን እና መርማሪ ፖሊስ እያቀረባቸው ያለው ሀሳቦች ተደጋጋሚና የተከሳሾችን የዋስትና መብት የሚጋፋ በመሆኑ ፖሊስ የጠየቀው ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ውድቅ በማድረግ የተከሳሾችን መዝገብ በመዝጋት በነፃ እንዲያሰናብታቸው ወይም ደግሞ የዋስትና መብታቸው እንዲጠበቅ ፍርድ ቤቱን ጠይቀዋል።
የግራ ቀኙን ክርክር ያዳመጠው ፍርድ ቤቱም በዛሬው ዕለት ቀጠሮ የተያዘው መርማሪ ፖሊስ   በተጠርጣሪዎች ላይ ያገኘውን ማስረጃ ሪፖርት ለማድመጥ አለመሆኑን ገልጾ መርማሪ ፖሊስ የጠየቀው ተጨማሪ የ28 ቀን የምርመራ ጊዜ ውድቅ በማድረግ ሁሉም ተጠርጣሪዎች የ15 ሺህ ብር ዋስትና በማቅረብ እንዲፈቱ ትዕዛዛ አስተላፏል።
በመጨረሻም መርማሪ ፖሊስና ዐቃቤ ህግ ፍርድ ቤቱ ለተከሳሾች የፈቀደው ዋስትና እንዲነሳ ይግባኝ ጠይቀዋል። መረጃው የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ነው፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *