ፓውል ማናፎርት ጥፋተኛ ሆነው ከተገኙ የ30 ዓመት እስራት ይጠብቃቸዋል፡፡
የቀድሞው የትራምፕ የምርጫ ቅስቀሳ ሀላፊ የነበሩት ማናፎርትን በችሎት ፊት ዋሽተዋል ብሏቸዋል አቃቤ ህግ፡፡ ባንክ ቤት ማጭበርበርን የሚለውን ጨምሮ በ18 ክሶች ተጠርጥረው ፍርድ ቤት የቀረቡት የቀድሞው የትራምፕ ባለሟል ራሳቸውን ከህግ በላይ አድርገው ይቆጥሩ እንደነበርም አቃቤ ህግ በክስ ዝርዝሩ አስረድቷል፡፡
ማናፎርት በውጭ ሀገራት በሚገኙ ባንኮች በ10 ሚሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር ማስቀመጣቸውም በክስ መዝገባቸው ላይ ተጠቅሷል፡፡
አቃቤ ህግ እንደሚለው ሰውየው በርካታ አካውንቶችን የከፈቱት በዋናነት ታክስ ለማጭበርበር እንዲረዳቸው በማሰብ ነው፡፡
ዘገባው የቢቢሲ ነው፡፡