loading
ፍርድ ቤቱ የኦነግ ታጣቂዎች ነን በማለት የህብረተሰቡን ሰላም ሲያውኩ ነበር ያላቸውን አራት ግለሰቦች በሦስት ዓመት ፅኑ እስራት ቀጣ

አርትስ 21/02/2011

 

የምዕራብ ወለጋ ዞን ባቦ ገንቤል ወረዳ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት አቶ መልካሙ ቦካ ለኢዜአ እንደተናገሩት በጽኑ እስራት እንዲቀጡ የተወሰነው ቡልቲነጊና ፣ በሊና ሸጪ ፣ አሰፋ ኢብሳና ፈቀደ ሻፊ በተባሉ ግለሰቦች ላይ ነው፡፡

ግለሰቦቹ መስከረም 22 ቀን 2011 ዓ.ም. በሽመል ቶኬ ከተማና በባቦ ገንቤል ወረዳ የተለያዩ ቀበሌዎች በመንቀሳቀስ የኦነግ ታጣቂዎች  ነን በማለትህብረተሰቡን በያዙት ስለታማ መሳሪያ እያስፈራሩ ዘረፋ ለመፈፀም ሲንቀሳቀሱ በህብረተሰቡና በወጣቶች ጥቆማ በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

ግለሰቦቹ ፀጉራቸው ላይ ዊግ በመቀጠልና የወታደር ልብስ በመልበስ የህብረተሰቡን ሰላም ሲያውኩ እንደነበር ፕሬዝዳንቱ ገልፀዋል ።

ምስክር ከተሰማባቸውና በቂ ማስረጃም ከተሰበሰበባቸው በኋላ ተከሳሾች መከላከል ባለመቻላቸው የወረዳው ፍርድ ቤት በዋለው ችሎት ጥፋተኛናቸው ብሏቸዋል፡፡

በዚህም መሰረት ተከሳሾች እያንዳንዳቸው በሶስት አመት ፅኑ እስራት እንዲቀጡ ፍርድ ቤቱ ወስኖ ቅጣቱን ያስፈፅም ዘንድ ወደ ምዕራብ ወለጋ ዞንማረሚያ ቤት ተልከዋል።

አቶ መልካሙ ህብረተሰቡ በእንዲህ አይነት ግለሰቦች ሰላሙን እንዳያጣና እንዳይጭበረበር ለሰላሙ ዘብ መቆምና የተለየ ነገር ሲያስተውልም ለፀጥታአካላት ጥቆማ መስጠት አለበት ብለዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *