ፈረንሳይ ለአዲስ አበባ የፅዳት ልምድ ልታካፍል ነው
አርትስ 03/02/2011
ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ የፈረንሳዩን አምባሳደር ፍሬድሪክ ቦንተምስን በፅ/ቤታቸዉ ሲያነጋግሩ የከተማዋ ቆሻሻ አንዱ ርዕሰ ጉዳያቸው ነበር ። በውይይታቸውም በከተማዋ የደረቅ ቆሻሻ አወጋገድ፣በአረንጓዴ ልማት እና በአካባቢ ጥበቃ ላይ በትብብር ለመስራት ተስማምተዋል።አምባሳደር ፍሬድሪክ የፈረንሳይ ከተሞች በፅዳት እና በስነ ህንፃ ውበት ዙሪያ ያላቸውን መልካም ተሞክሮ ለአዲስ አበባ ለማካፈል እና በሰው ሀይል ስልጠና ላይ ለመዲናዋ ድጋፍ ለማድረግ ፈረንሳይ ፍላጎት እንዳላት መናገራቸውን የከንቲባ ፅ/ቤት አስታውቋል።